የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 46.2 ሚሊዮን ትርፉ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ደርሷል

  • ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።
የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝተናል ብለዋል።
ከትርፉ ላይም 11 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ግብር ከፍያለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም 318 ነጥብ 4 ሚሊየን እዳንም ከፍያለሁ ብሏል።
እንደ ወ/ት ፍሬህይወት የተገኘው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ31 ነጥብ 4 መቶ ብልጫ አለው ።
በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 46.2 ሚሊዮን ደርሷልም ብለዋል።
የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 44.5 ሚሊዮን፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 23.8 ሚሊዮን፣ የብሮድባንድ ደንበኞች ብዛት 212.2 ሺ እንዲሁም የመደበኛ ስልክ 980 ሺ ደንበኞች አሉትም ተብሏል።
Source – ኢትዮ ቴሌኮም