የህግ የበላይነት የሚረጋገጠው እና ፍትህን ለማስፈን የሚተጋው እንደ አማራጭ ሳይሆን የሃገሪቱን እና የህዝቡን የህልውና ዋና መሰረት መሆኑን በመረዳት ነው – ወ/ሮ አዳነች አቤቤ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
በህግ የተጀመረው ስራ በህግ የሚጨረስ መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው- ጠ/ዐቃቤ ህግ ወ/ሮ አዳነች
(ኤፍ.ቢ.ሲ) የህግ የበላይነት ማክበር፣ ማስከበር እና ፍትህን ማስፈን የህልውናችን መሰረት ነው ሲሉ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ህግ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገለፁ።
የህግ የበላይነት እና ፍትህ እንዲሰፍን ዘርፈ ብዙ ስራ እና ርብርብ ላይ እየተደረገ እንደሚገኝ በፌስቡክ ገፃቸው ላይ አስፍረዋል።
በኢትዮጵያ ፍትህ እንዲሰፍን የበሚደረገው ርብርብ ሁሉም ሰው በህግ ፊት እኩል እና ከህግ በታች መሆኑን ለማረጋገጥ በህግ የተጀመረው ስራ በህግ የሚጨረስ መሆኑን መረዳት ተገቢ ነው ብለዋል።
የተለያዩ ሃላፊነት የጎደላቸው እና ከእውነት የራቁ እንቅስቃሴዎች፣ ንግግሮች፣ መግለጫዎች በራስ ወዳድነት፣ ለግላዊ ጥቅም፣ ለርካሽ ተወዳጅነት እና ለዝና የሚደረጉ ድርጊቶች ለብዙ ጥፋት እና ጉዳት እንደሚዳርጉ በአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ሞት ሳቢያ የተፈጠረው ጊዜያዊ ረብሻ ማሳያ ሆኗልም ነው ያሉት።
ከአሁን በኋላም የህግ የበላይነት የሚረጋገጠው እና ፍትህን ለማስፈን የሚተጋው እንደ አማራጭ ሳይሆን የሃገሪቱን እና የህዝቡን የህልውና ዋና መሰረት መሆኑን በመረዳት ነው ብለዋል ጠቅላይ ዐቃቤ ህጓ ።