ጠ/ሚ ዐቢይ በፈረንጆቹ 2020 ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።
ጠ/ሚ ዐቢይ በፈረንጆቹ 2020 ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በፈረንጆቹ 2020 ከ100 ስመ ጥር አፍሪካውያን መካከል አንዱ ሆነው ተመረጡ፡፡
ሪፒዩቴሽን ፖል ኢንተርናሽናል የተሰኘው ተቋም የፈረንጆቹ 2020 በተለያዩ የሙያ መስኮች ስመ ጥር የሆኑ 100 አፍሪካውያንን ዝርዝር ይፋ አድርጓል፡፡

(ኢዜአ) የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ አህመድ በፈረንጆቹ 2020 ጎላ ብለው ከታዩ አፍሪካውያን ተጽዕኖ ፈጣሪዎች መካከል አንዱ ሆኑ።
‘ሬፑቴሽናል ፖል’ የተባለው ተቋም ጠቅላይ ሚኒስትርዓቢይን ከ100 አፍሪካውያን መካከል አንዱ አድርጓቸዋል።
‘ቢዝነስ ኒውስ ሪፖርት’ ድረ ገጽ እንዳሰፈረውዶክተርዓቢይ ከ47 ሴትና 53 ወንድ በድምሩ100አፍሪካውያን ዝርዝር ውስጥ ተካተዋል።
አፍሪካውያኑ በአመራርነት፣ በመዝናኛው፣ በትምህርትና በንግድ ዘርፎች ባከናወኑት ተግባራት እንደሚካተቱና መስፈርቱም ተጽዕኖ ፈጣሪነት፣ ጎልቶ መታየትና ሐቀኝነት መሆኑን ድረ ገጹ አስፍሯል።
ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ በተጨማሪ በንግድ ዘርፍ ኢትዮጵያዊቷ ‘የሶል ሬብልስ’ ባለቤት ቤተልሄም ጥላሁን በዝርዝሩ ውስጥ ተካታለች።
የዘላቂ ልማት ግቦች የአፍሪካ ማዕከል ዳይሬክተር ጄኔራል በላይ በጋሻውም ሌላው በዝርዝር ውስጥ የተካተተ ሌላው ኢትዮጵያዊ ነው።
በዝርዝሩ ውስጥ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዓቢይ በተጨማሪ የሩዋንዳው ፕሬዚዳንት ፖል ካጋሜና የአፍርካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን ዋና ፀሓፊ ካሜሩናዊቷ ዶክተር ቬራ ሶንግዌ ይገኙበታል።
በተጨማሪም ናይጄሪያውያኑ ዶክተር ፖል አንቼቼና ንጎዚ ኦንኮቾ-ኢዌላ፣ ደቡብ አፍሪካዊው ፕሮፌሰር ዋይዝማን ንኩሉ፣ ጊኒያዊው ኢኮኖሚስት ኬሉ ዳሊኤን የመሳሳሉ ተዕፅኖ ፈጣሪ አፍሪካውያን ተካተውበታል።
‘ሬፑቴሽናል ፖል’ ተቋም በየዓመቱ ግልጽነትና ሐቀኝነትን ማዕከል አድርጎ ጎልተው የታዩ ሰዎችን ዝርዝር ያወጣል።