የራስን እድል በራስ የመወሰን መብት ለናዝሬት/አዳማ #ግርማካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በናዝሬት/አዳማ ባለፈው የሕዝብ ቆጠራ፣ 74% የሚሆኑት ነዋሪዎች ኦሮምኛ ተናጋሪ አይደሉም። ሆኖም በከተማዋ አስተዳደር ፣ በቀበሌዎች የሚቀጠሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ብቻ ናቸው። የከተማዎ ፓሊስ ሆነው የሚሰሩት አብዛኞቹ የአዳማ/ናዝሬት ተወላጆች አይደሉም፡፡ ከሌላ ቦታ የመጡ ናቸው፡፡ ኦሮሞዎችም ኦሮምኛ የማይናገሩ ከሆነ በከተማዋ ቦታ የላቸውም፡፡

አቶ አብርሃም አዶሌ፣ አቶ በከር ሻሌ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽ፣ አቶ ጉቱ፣ አቶ ጀማል አባስ፣ አቶ ሀብታሙ ሃይለሚካኤል፣ ወ/ሮ አዳነች አበቤ፣ አቶ አሰገድ ጌታቸው …ሁሉም የአዳማ ከተማ ከንቲባ ሆነው የሰሩት ኦሮምኛ ተናጋሪ ኦሮሞዎች ናቸው። አንዳቸውም በአዳማ ከተማ ሕዝብ አልተመረጡም። በቀጥታ በኦሮሞ ክልል ርእስ መስተዳደሮች ነው የተሾሙት። የአሁኑ የአዳማ ከንቲባ አቶ አስገድ ጌታቸውና ከአቶ አሰግድ በፊት የነበሩት ወ/ሮ አዳነች አበቤን የሾሙት አቶ ለማ መገርሳ ነበሩ።

ከነዚህ ከንቲባዎች ደግሞ ጥቅት የማይባሉ ቢያንስ ወደ ስድስት ከንቲባዎች በሙስና በዘረፋ ከሃላፊነታቸው ተነስተዋል። አቶ ጉቱ፣ አቶ ሲሳይ ነጋሽን እንደ ምሳሌ መጥቀስ ይቻላል።

የናዝሬት/አዳማ አብዛኛው ኦሮምኛ የማይናገር ነዋሪ ከከተማዋ መስተዳደር መንግስታዊ አገልግሎት የማግኘት ችግር አለበት። ጉዳዮችን ለማስፈጸም ሰነዶችን ፣ ፎርሞችን ለአስተርጓሚ ከፍሎ አስተርጉሞ ነው የሚያቀርበው፡፡ ደብዳቤዎችን ወደ ላቲን/ቁቤ ለማስቀየር ለተርጓሚዎች በገጽ መቶ፣ ሁለት መቶ ብር ነው የሚክፈለው።

በአጭሩ አነጋገር የናዝሬት/አዳማ ከተማ ሕዝብ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብት የለውም።አንድ በናዝሬት የተወለደ፣ እናቱ አባቱ በናዝሬት የተወለዱ ኦሮምኛ የማይናገር የናዝሬት ነዋሪ ካለው መብት ይልቅ፣ ከአርሲና ወለጋ ከመጡ ስድስት ወራት የሆናቸው ኦሮምኛ ተናጋሪዎች የበለጠ መብት አላቸው። ይሄም በአዳማ ያለው አሰራር አፓርታይዳዊ አሰራር መሆኑን ነው፡፡

እዚህ ሊሰመርበት የሚገባው ራሱን የለዉጥ ኃይል የሚለው፣ የብልጽግና ፓርቲ እንደ ናዝሬት/አዳማ ባሉ አካባቢዎች ያሉ ኢፍታዊ፣ ዘረኛና የአብዛኛውን ነዋሪን መብት የሚረግጥ አሰራር ያስተካክላል የሚል ግመት በብዙዎች ዘንድ ነበር፡፡ ሆኖም እንኳን ሊያስተክክል እንደዉም በትጋት እያስቀጠለ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው፡፡

ናዝሬት/አዳማ ትልቅ ፖቴንሻል ያላት ከተማ ናት። ሕዝብ የመረጠው፣ ለሕዝብ የቆመ የከተማ መስተዳደር ቢሰፍን፣ ህዝብ በፈለገ ጊዜ ለከተማችን አልሰሩም የሚላቸውን መሻርና በመትካቸው ሌሎች መሾም ቢችል አዳማ የትናየት ትደርስ ነበር።