የወላይታ ዞን ምክርቤት የደቡብ ልዩ ሀይል ዞንኑ ለቆ እንዲወጣ ዛሬ በረገው አስቸኳይ ስብሰባ ወሰነ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


የወላይታ ዞን ም/ቤት 4ኛ ዙር 7ኛ የሥራ ዘመን 2ኛ አስቸኳይ ጉባኤ መርሀ ግብር ላይ በሰባት ነጥብ የተነሱ አጀንዳዎች ላይ በሙሉ ድምጽ አፀደቀ።
1- የዎላይታ ህዝብ የጠየቀው በክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ ጥያቄ ብቻ ነው። ከዚህ ውጭ የሚመጣ ማንኛውንም አይነት ምላሽም ሆነ ውሳኔ ምክር ቤቱ የማይቀበል መሆኑን እና መንግስት የህዝባችንን ጥያቄ በአጭር ጊዜ ውስጥ ህገ መንግስታዊ መንገድን ትከትሎ ህጋዊ ምላሽ እንዲሰጥ፤
2- የፌዴሬሽን ምክር ቤት በአጭር ጊዜ ውስጥ ህዝበ ውሳኔ እንዲያደራጅ ለምርጫ ቦርድ ውሳኔ ሰጥቶ እንዲያስተላልፍ። ይህ ካልሆነ ግን ለሚፈጠረው ማንኛውም አይነት ችግር ማዕከላዊ መንግስት ኃላፊነት መውሰድ እንዳለበት፤
3- በደቡብ ክልል ምክር ቤት የህዝባችን ጥያቄ አልተመለሰም/ታፍኗል በሚል መልቀቂያ አስገብተው የወጡ ተወካዮቻችን ላይ የሚወሰድ የትኛውም ውሳኔ ተቀባይነት እንደሌለው እና የደቡብ ክልል ምክር ቤት ከአሁን በኃላ ተወካዮቻችን በሌሉበት ሁኔታ የዎላይታ ህዝብን ሊወክሉ የሚችሉ አጀንዳዎች ጉዳዮችን ማየትም ሆነ ውሳኔ መስጠት እንደማይችል፤
4- የሠላምና የፀጥታ ጉዳያችን ላይ የአካባቢያችን ፖሊስ፣ ሚልሻ፣ ወጣቶችና የዎላይታ ህዝብ በጋራ ክንድ ተባብሮ እንደሚሰራ እንዲሁም አስፈላጊ በሆኑ ጉዳዮች የፌደራል ፖሊስ ከህዝባችን ጋር አብሮ እንድሰራ ነገር ግን የደቡብ ክልል ልዩ ሀይል ከአሁን በኃላ በአካባቢያችን የሠላምና የፀጥታ ጉዳይ እንደማይመለከተውና ከአካባቢያችን መውጣት እንዳለበት፤
5- በክልል የመደራጀት ህገ መንግስታዊ ጥያቄያችን በህዝብ ጥንካሬና ትግል መመለሱ ስለማይቀር ምክር ቤቱ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን በማደራጀት የቅድመ ዝግጅት ስራ መጀመር እንዳለበትና ይህን ሥራ በበላይነት የሚመራ ጽ/ቤት እንድቋቋም፤
ከጽ/ቤቱ ተግባራት በከፊል፥
~የወላይታ ባንድራ ምን መሆን እንዳለበት፣
~የወብክመ ህገ መንግስት ምን መሆን አለበት የምለው ረቂቅ እንድዘጋጅ፣
የሚቋቋመው ጽ/ቤት በነዚህ እና መሰል ጉዳዮች በቀጣይ ወላይታን የሚመለከቱ ፖለቲካዊ፣ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጉዳዮችን በመተንተን ፖሊስዮችንና ስትራቴጂ የሚያቀርብ እንድሆን ውሳኔ አስተላልፈዋል፤

6- አሁንም እንደ ቀድሞ ሁሉ የክልል ጥያቄያችንን ሰላማዊና ሰላማዊ መንገድን ብቻ በመከተል ትግል ማድረግ እንደሚገባ፤

7- ከጎረቤት ህዝቦች ጋር ያለንን የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር እንደሚገባ እንዲሁም
የዎላይታ ህዝብን ከወንድም ህዝቦች ጋር ለማጋጨት ድብቅ የፖለቲካ ሴራ አንግበው የሚንቀሳቀሱ ሀይሎችን በማውገዝ በሙሉ ድምጽ የቀረቡ አጀንዳዎች ላይ ውሳኔ አስተላልፈዋል።
የወላይታ ሕዝብ የኢትዮጵያ ሕገመንግሥት ከጸደቀና ሥራ ላይ ከዋለ ጀምሮ የክልልነት ጥያቄ ሲያነሳ ቆይቷል። ይሁንና በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 47/2 ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች በማንኛውም ጊዜ የራሳቸውን ክልል የማቋቋም መብት እንዳላቸው የተደነገገ ቢሆንም ይህ ሕገ-መንግሥታዊ መብት ተግባራዊ ሳይሆን 27 ዓመታት ተቆጥረዋል። በነዚህ ዓመታት ይህ ሕገ-መንግሥታዊ መብት ተግባራዊ እንዲሆን የወላይታ ሕዝብ ታግሏል፤ መስዋዕትነትም ከፍሏል።
በቀደምት አርበኞች እግር እንደ መተካታችን፣ እኛ የዚህ ትውልድ አባላትም የአንድነት፣ የሰላም እና የሉዓላዊነታችን ፋና ወጊዎች ነን። እናቶቻችን እና አባቶቻችን የወሰኑት ታሪካዊ ውሳኔና ለሰባት አመት ያደረጉት እልህ አስጨራሽ ጦርነት ለነጻነት፣ ራስን በራስ የማስተዳደር ሉዓላዊ ሕዝብ ከምንም በላይ መሆናቸውን አሳይቶናል።