ቀይዋ መፅሐፍ – የሀገራችን መከላከያ ሰራዊት ቅዱስ መፅሐፍ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ቀይዋ መፅሐፍ” (The Red Book)
===Oluma M. Wodajo =====
ጠሚው በእጃቸው የያዝዋት በተለምዶ “ቀይዋ መፅሐፍ” ተብላ ትታወቃለች። የቀድሞው ጠሚ መለስ ዜናዊ ናቸው ከ93ቱ ክፍፍል በኋላ ብቻቸውን በር ዘግተው የፃፏት።
ጄ/ል ሳሞራ በጡረታ እስከተሰናበቱባት ዕለት ድረስ የሀገራችን መከላከያ ሰራዊት “ቅዱስ መፅሐፍ” ነበረች።
Image may contain: 1 person200 ገፆች ያላት ይህቺ መፅሀፍ በስምንት ቃላት ስትጠቃለል “መከላከያ ሰራዊቱ የአብዮታዊ ዴሞክራሲ ስርአታችን የመጨረሻ ምሽግ ነው” ትላለች።
በህገ-መንግስቱ አንቀፅ 87 የሰፈረውን “መከላከያ ሰራዊቱ ከማንኛውም ፖለቲካዊ ወገንተኝነት የፀዳ መሆን አለበት” የሚለውን መርህ ያለማቅማማት ትጥሳለች። ይሁንና እስከ ለውጡ እለት ድረስ የሀይማኖትን ያህል ከህገ-መንግስቱ በላይ ተፈርታ እና ተከብራ ዘልቃለች።
ዛሬስ?…መቼም ጠሚው ሊያንቆለጳጵሷት ሳይሆን “ጥምብ-እርኩሷን ሊያወጡት” እንደያዟት መጠርጠር አይከብድም።
እርሳቸውም ግን ካሁን በኋላ የሀገር መከላከያ ሰራዊት የፖለቲካ ፓርቲ አለኝታ ያይደለ ጠንካራ ሀገራዊ ተቋም ይሆን ዘንድ እቅድ አውጥተው እንደሚያስፈፅሙ ተስፋ እናደርጋለን።