“ፈንቅል” በሚል ስም ለፍትህ የሚኦደረግ ጸረ-ሕወሃት ን ትግራይ እያጥለቀልቀ ነው #ግርማካሳ

Updates from Tigray
“ፈንቅል” በሚል ስም ለፍትህ የሚኦደረግ ጸረ-ሕወሃት ን ትግራይ እያጥለቀልቀ ነው #ግርማካሳ

ሕወሃትና የክልሉ መንግስት በአንድ በኩል የፌዴራል መንግስትን ከሚቆጣጠረውና በዶር አብይ አህመድ ከሚመራው የብልጽግና ፓርቲ የፖለቲካ ውዝግብ ውስጥ መግባቲ ይታወቃል። በድርጅቱ ውስጥ ከፍተኛ ልዩነቶችን መከፋፈለኦች እንዳሉ እየተነገረ ነው። ሆኖፕም ኅወሃት በውስጡ ካሉ መከፋፈሎችና ከፌዲርል መንግስቱ ጋር ካለው ችግር በባሰ ሁኔታ ግን ለሕልውና ትልቅ አደጋ እየፈጠረበት ያለው በትግራይ የተነሳው መጠነ ሰፊ ሕዝባዊ ተቃውሞዎች ናቸው።

በተለይም በወጣቱ ድጋፍ እንደሌለው የሚነገርለት ኅወሃት በየወረዳውና በየቀበሌው ባሰማራቸው ታጣቂዎቹና ካድሬዎቹ፣ የክልል መንግስት እንድመሆኑም ባለው የመንግስት መዋቀር ላይ በተቀመጡ ሃላፊዎቹ አማካኝነት ህዝቡብ በማስፈራራት፣ በማፈን ፣ በጉልበትና በጫና የኅዝብን መስረታዊ የፍትህ፣ የሰላምና የልማት ጥያቄዎችን ለመጨፍለቅ ደፋ ቀና እያለ ነው።

በዚህ ሳምንት ውስጥ ብቻ በትግራይ ያሉ ብርካታ አውራጃዎችና ከተማዎች ተቃውሞን ሲያስተናግዱ ነበር። ሌላው ቢቀር ኅወሃት ተወለድችበት በሚባለ በሬ/ደደቢት እኗን ሳይቀር ጸረ-ሕወሃት ተቃውሞ ሲሰማ ነበር። ተቃውሞኢ ሲደረግባቸው ከነበሩት ጥቂቶቹን እንደሚከተው ቀርበዋል፡

እንደርታ/መቀሌ

የትግራይን ሕዝብ የማይወክሉ ለጥቅማቸው የቆሙ የሕወሃት ሰዎች የሚያደርሱን ግፍነ በደል በመቃወም በተነሳው ተቃውሞ የክልል መንግስትይ ታጣቄዎች በሰላማዊ ዜጎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል። ሁለተ የመቀሌ ወጣቶች ሲሞቱ ብዙዎች ቆስለዋል።

እንደርታ/ወጀረት
“በተፈቀደ የወረዳነት ጥያቄ ህዝብ መሃል ገብታቹ ልዩነት ለመፍጠርና ወደ ኋላ ለመመለስ እያካሄዳቹ ያላቹ ተንኮል ኣቁሙ” በማለት ዛሬ ቅዳሜ ተቃውመው ኣሰምተዋል።

ህወሓት የተመለሰ ጥያቄ ወደ ስራ እንዳይገባ በህዝቡ መሃል ገብታ እያጣላች መሆንዋ በመንቃቱ ተግባርዋ ኣምርሮ እየተቃወመ ይገኛል።

በተመሳሳይ የማይሓንሰ ደደቢት ህዝብ በሰለማዊ ሰልፍና መንገድ በመዝጋት እያሰማ ያለው ተቃውሞ 7 ቀኑ ይዘዋል።

እንደርታ/ሂዋነ

ሂዋነ በመቀሌና ማይጨው መካከል ያለች ከተማ ናት። ነዋሪዎቹ የሚመለከትቸው ሃላፊዎች አስጠርተው፣ ተቃዉሟቸው አቅርበዋል። የክልል አመራሮች መጥተው እንዲያነጋገሩቸው ላቀረቡት የትህ ጥያቄ ምላሽ እንዲሰጡም ጠየቅዋል። ያ ካለሆነ ግን ፍትህ የተጠማው ህዝብ ወደ ሚቀጥለው ደረጅ እንደሚንቀሳቀስም አስጠንቅቀዋል።

ሽሬ/ማይሓንሰ ደደቢት

በሽሬ፣ ማይሓንሰ ደደቢት ቃውሞዎች ተቀስቅሰዋል። ሕዝቡም መንገዶችን ሁሉ እስከ መዝጋት የደረሰበት ሁኔተ ተፈጥሯል።፡ ከላይ እንደተጠቀሰው ደደቢት ሕወሃት ትግል ጀምሪበታለሁ የምትለው ከተማ ናት። ሆኖም ግን ሕወሃቶች ደደቢትን የሚያስታውሱት ለፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ በየአመቱ ሕወሃትን ትግል ጀመረ የተባለበት በዓል ለማክበር ብቻ ነው። ከዚያ ባለፈ አሁን ሕዝቡ በችግርና በድህነት፣ መብቱ ተርግጦ ነው የሚኖረው።

ክዙህ በታች ያለው ዛሬ በወጀራት፣ እንደርታ የተደርገው ተቃውሞ ነው !!!!