1441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ነገ ካልሆነ ግን ከነገ በስቲያ እንደሚከበር ታውቋል

1441ኛው የኢድ አል-ፈጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ነገ ካልሆነ ግን ከነገ በስቲያ እንደሚከበር የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት አስታውቋል! በዕለቱ የጀምዓ ሶላት እንደማይኖር ተቀዳሚ ሙፍቲ ሐጅ ኡመር ተናግረዋል።

የጠቅላይ ምክር ቤቱ ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሃጂ ኡመር እንድሪስ 1 ሺህ 441ኛውን የኢድ አል ፈጥር በዓልን በማስመልከት መልእክት አስተላልፈዋል።
በመልእክታቸውም ህዝበ ሙስሊሙ የዘንድሮውን የኢድ በዓል ሲያከብር የኮሮናቫይረስ የተከሰተበት ወቅት በመሆኑ በሽታው እንዳይሰራጭ ጥንቃቄ ማድረግ ይኖርበታል ብለዋል።
በመሆኑም ሁሉም የኢድ ሰላትን በየቤታቸው ሆነው እንዲሰግዱ አሳስበዋል።
በዓሉ ሲከበርም የተቸገሩትን በመርዳት፣ በመተጋገዝና በመተዛዘን እንዲሁም አንድነትን በሚያጠናክር መልኩ መሆን ይኖርበታል ብለዋል።
1 ሺህ 441ኛው የኢድ አልፈጥር በዓል ዛሬ ምሽት ጨረቃ ከታየች ቅዳሜ ዛሬ ካልታየች እሁድ ተከብሮ የሚውል መሆኑንም ገልጸዋል።
የዘንድሮው የኢድ በዓል የሚከበረው መንግስት ለህዝበ ሙስሊሙ በአዲስ አበባ ዓለም አቀፍ መስጂድና ኢስላማዊ ማዕከል የመስሪያ ቦታ ባስረከበ ማግስት መሆኑንም ጠቅሰዋል።
በዚህም በሙስሊሙ ማህበረሰብ ስም ለመንግስት ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
በመጨረሻም ለመላው የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮች “እንኳን ለ1 ሺህ 441ኛው የኢድ አል ፈጥር በዓል አደረሳችሁ” ብለዋል።

 መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV