በሐረሪ ክልል በኮሮና የተያዘ አንድ ሰው ተገኘ- ይኸ በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 399 ያደርሰዋል።

የጤና ሚኒስቴር ማምሻውን ባወጣው መግለጫ ተሕዋሲው የተገኘባቸው የ37 አመት የሐረር ከተማ ነዋሪ ከዚህ ቀደም ከኢትዮጵያ ውጪ ተጉዘው የማያውቁ በበሽታው ከተያዘ ሰውም ግንኙነት የሌላቸው ናቸው። ይኸ በኢትዮጵያ በኮሮና የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 399 ያደርሰዋል። እስካሁን ከጋምቤላ ክልል ውጪ በሁሉም የከተማ አስተዳደሮች እና ክልሎች በኮሮና የተያዙ ሰዎች ተገኝተዋል።መረጃ ቲቪን በተሻለ ጥራት እና ፍጥነት እንድናቀርብ እገዛችሁን እንሻለን።
መረጃ ቲቪን ለማገዝ ይህን ሊንክ በመጫን አባል ይህኑ - JOIN Mereja TV