የተመድ ዋና ፀሀፊ ኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን የፈረሙትን የመርሆች ስምምነት መሰረት ባደረገ መልኩ ያልተስማሙባቸው ጉዳዮችን ለመፍታት እንዲሰሩ ጠይቀዋል።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Image may contain: 1 person, closeupየተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ኢትዮጵያ፣ግብፅ እና ሱዳን በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙርያ ያላቸውን ልዩነቶች ሰላማዊ በሆነና የጋራ ተጠቃሚነትን ባከበረ መልኩ እንዲፈቱት መጠቃቸው ተሰማ።
ዋና ፀሀፊዉ በህዳሴ ግድብ ዙርያ የሚደረጉ ድርድሮችን በቅርበት መከታተላቸውን እንደሚቀጥሉ ተናግረው የእስካሁኑንም ሂደት የሚበረታታ ነው ብለውታል።
አሁንም ሶስቱ አገራት ድርድራቸውን እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2015 በተፈራረሙት የመርሆች ስምምት መሰረት ሊቀጥሉ ይገባል ብለዋል።
የዛሬ 5 ዓመቱ የመርሆች ስምምነት የጋራ ተጠቃሚነት፣በቀና መንፈስ ፣ ፍትሃዊነትን ባሰፈነ ሁኔታ እንዲሁም አለም አቀፍ ህጎችን ዋና መሰረቱን ያደረገ መሆኑን የአንቶኒዮ ጉተሬዝ አንስተዋል።
ዋና ፀሀፊው አገራቱ የፈረሙትን የመርሆች ስምምነት መሰረት ባደረገ መልኩ ያልተስማሙባቸው ጉዳዮችን ለመፍታት እንዲሰሩም አክለው ጠይቀዋል።
ግብፅ የግድቡን ጉዳይ ከሳምንታት በፊት ወደ ተባበሩት መንግሥት ድርጅት የፀጥታ ጥበቃው ምክር ቤት መውሰዷ ይታወሳል።