" /> የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተወሰነ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ተወሰነ

የዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ መወሰኑን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ተናገረ።ሚኒስቴሩ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታትና ተማሪዎች በቫይረሱ ምክንያት የከፋ ችግር እንዳይደርስባቸው በማሰብ መሆኑን ኃላፊዎቹ ለመንግሥታዊ መገናኛ ብዙኃን ተናግረዋል።
ይሁን እንጂ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማቱ ከአንድ ቀን በፊት በተላለፈላቸው ውሳኔ መሠረት የቫይረሱን ሥርጭት ለመግታት ሲባል ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ መውጣት አይችሉም ሲሉ ማስታወቂያ ለጥፈው እንደነበር ይታወሳል።ዋቸሞ እና አሶሳ ዩኒቨርስቲዎች በማደሪያ ክፍል መጣበብ እንዳይኖር ተማሪዎችን ግንባታቸው ወደተጠናቀቀላቸው ሕንጻዎች እያሸጋሸጉ መሆናቸውን ለሸገር መናገራቸው አይዘነጋም።
ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው በሚመለሱበት ጊዜ መጓጓዣ የማመቻቸት ኃላፊነት የዩኒቨርሲቲዎች ነው ተብሏል።የሚኒስቴሩ የሥራ ኃላፊዎች ተማሪዎቹ መቼ ወደ ትምህርት ገበታቸው እንደሚመለሱ አልተናገሩም።ቀደም ሲል ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲዎቻቸው እንዲቆዩ ተወስኖ የነበረው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን በመፍራት እንደነበር የሚታወስ ሲኾን፣ ሚኒስቴሩ አሁን የተማሪዎቹን ወደቤተሰብ መመለስ ለመፍቀዱ በምክንያትነት የጠቀሰውም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ፍራቻን መሆኑን ለማወቅ ተችሏል።ተማሪዎች ወደየቤተሰቦቻቸው እንዲሄዱ ሲፈቀድ፣ የሚገኙበትን የጤንነት ሁኔታ ለማጣራት የሚሠራ ሥራ ስለ መኖር አለመኖሩ ኃላፊዎቹ የተናገሩት ነገር የለም።
Source -የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር 

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV