" /> የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞች ከነገ ጀምሮ በቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞች ከነገ ጀምሮ በቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ወሰነ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞች ተጨማሪ ማብራሪያ እስኪሰጥ ድረስ ከነገ ጀምሮ በቤታቸው ሆነው እንዲሠሩ ወሰነ
የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮቪድ19 ገደብ የለሽ ስርጭት ሊያስከትል የሚችለውን ማኅበራዊ፣ ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ውዥንብር ለመከላከል የሚወሰዱ እርምጃዎችን በተመለከተ አስቸኳይ ስብሰባ አካሂዷል።
ዛሬ ጠዋት ባካሄደው ስብሰባ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ይቻል ዘንድ የሚኒስትሮች ምክር ቤት የፌዴራል መስሪያ ቤት ሠራተኞች ተጨማሪ ማብራሪያ እስኪሰጥ ድረስ ከነገ ጀምሮ በቤት ውስጥ ሆነው እንዲሠሩ ወስኗል።
እቤት ቁጭ ብለው የሚሠሩ የመንግሥት ሠራተኞች የየሚኒስቴር መሰሪያ ቤቶቹ በሚያወጡት መመሪያ ማን እቤት ሆኖ እንደሚሠራ እንደሚወስኑም ምክር ቤቱ አመልክቷል።
ቤት ሆነው የሚሠሩ ሠራተኞች የሚፈለግባቸውን አገልግሎት በኃላፊነት ስሜት መሥራት እንዲችሉ ራሳቸውን ዝግጁ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸውም ተመልክቷል።
ውሳኔው የተላለፈው በአዲስ አበባ የሚኖረውን የትራንስፖርት ጭንቅንቅ ለመቀነስ ታስቦ መሆኑንም ምክር ቤቱ አመልክቷል።
ምክር ቤቱ ዛሬ በካሄደው 17ኛው አስቸኳይ ስብሰባ የቫይረሱን ስርጭት ለመግታት እንዲቻል ተጨማሪ ንዑሳን ኮሚቴዎች ማዋቀሩንም አስታውቋል።

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV