" /> አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ለደረሰባት ኪሰራ ማገገሚያ የዕዳ ስረዛ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግስት ጠየቀ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ለደረሰባት ኪሰራ ማገገሚያ የዕዳ ስረዛ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግስት ጠየቀ

አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ለደረሰባት ኪሰራ ማገገሚያ የዕዳ ስረዛ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲደረግ የኢትዮጵያ መንግስት ጠየቀ።የኢትዮጵያ መንግስት የቡድን አባል አገራትንና የዓለም ባንክ ለተላከላቸው ሰነድ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ጠይቋል። ሰነዱ ከታች ተያይዟል።
ኢትዮጵያ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ለደረሰባት ጉዳት ማካካሻ የሚሆን እርምጃ እንዲወሰድ የዓለም ባንክን እና የቡድን 20 አባል አገራትን ጠየቀች።
ጠቅላይ ሚኒስቴር ጽህፈት ቤት እንዳለው የቡድን 20 አባል አገራት እና የዓለም ባንክ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ለደረሰባት ኪሰራ ማገገሚያ የዕዳ ስረዛ፣ የገንዘብ ድጋፍ እና ሌሎች የህክምና ቁሳቁሶች ድጋፍ እንዲደረግ የሚጠይቅ ሰነድ ተዘጋጅቷል።
እንደዚህ ሰነድ ከሆነ አፍሪካ በዚህ ገዳይ ቫይረስ ሳቢያ የወጪ ንግድ ቆሟል፣ኢኮኖሚያዊ አንቅስቃሴዎች ቆመዋል፣የስራ እድል አሽቆልቁሏል እና ሌሎች ጉዳቶች በአፍሪካ ላይ ጉዳት ደርሷል።በዚህ ሳቢያም አፍሪካ ይሄንን ቫይረስ መከላከል የሚያስችላትን የገንዘብ፣የህክምና ቁሳቁስ እና ሌሎች ድጋፎችን ልታገኝ ይገባል ተብሏል።በዚህ ሳቢያ የዓለም ባንክ እና ሌሎች ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ድርጅቶች ለአፍሪካ አገራት ያበደሩትን ብድር እንዲሰርዙ እና የመክፈያ ጊዜ እንዲያራዝሙም የኢትዮጵያ ሰነድ ይጠይቃል።
Image
Image

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV