" /> አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊትያስፈልገናል። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊትያስፈልገናል።

አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊትያስፈልገናል።
በየቦታው የምናያቸው የሕዝብ እንቅስቃሴዎች ለኮሮና ቫይረስ መስፋፋት አስጊ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ መንግስት በመጭው ሳምንታት በመቶዎች የሚቆጠሩ የኮሮና ታማሚዎች እንደሚኖሩን እየተናገረ መሆኑ እየተሰማ ባለበት በዚህ እጅግ አደገኛ በሆነ ወረርሽን ለመጠቃት በተዘጋጀንበት አደገኛ ወቅት ላይ በሕገመንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀጽ 1/ሀ መሰረት መንግስት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ሊያውጅ ይገባል።
በመቶዎች የሚቆጠሩ ታማሚዎችንና ሞትን ከማስተናገዳችን በፊት የዜጎችን ደሕንነትና ሰላም የመጠበቅ ኃላፊነት የመንግስት ግዴታ ነው።
NB : ኮሮናቫይረስ በኢትዮጵያ በ11 ሰዎች ላይ የተገኘ ቢሆንም በቀጣዮቹ ቀናት በመቶዎች ሊያድግ ስለሚችል ሁሉም ሰው በተረጋጋ ሁኔታ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥሪ አቅርበዋል።
ሕገመንግስቱ አንቀፅ 93 ንዑስ አንቀጽ 1/ ሀ
…………… የሕዝብን ጤንነት አደጋ ላይ የሚጥል በሽታ ሲከሰት የፌዴራሉ መንግስት የሚኒስትሮች ምክር ቤት የ አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የመደንገግ ስልጣን አለው ። ……… ለክልሎችም በንዑስ አንቀጽ 1/ለ ላይ ይህ ስልጣን ተሰጥቷቸዋል።MinilikSalsawi

የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV