" /> ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኮቪድ19ን ስርጭትን አስመልክቶ ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ የኮቪድ19ን ስርጭትን አስመልክቶ ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የኮቪድ19ን ስርጭት ለመግታት የሚደረግ የዝግጅት ሥራን አስመልክቶ፣ ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል።

ጠ/ሚር ዐብይ አህመድ የሚከተሉት እርምጃዎች እንደሚተገበሩ ዛሬ ይፋ አድርገዋል

1. ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን አንስቶ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰው የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎች የሚያስቆም እና ማሕበራዊ ርቀትን መጠበቅን የሚያስተገብር ይሆናል።
2. የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የመንግሥት ተቋማት ርቀትን ተፈጻሚ ማድረግ እና ስብሰባን ሲያካሂዱ ቫይረሱን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው።
3. የመንግሥት ተቋማት የተቀጣሪዎቻቸውን ሁኔታ በማጣራት እንደየሁኔታው አንዳንዶች በቤታቸው ሆነው የሚሰሩበትን መንገድ ማመቻቸት።
4. የሕዝብ መጓጓዣ አገልግሎት ሰጪዎች አጨናንቆ ተሳፋሪዎችን መጫን የማይችሉ ሲሆን ይህን ማድረጋቸው በትራፊክ ፖሊስ እና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ቁጥጥር የሚደረግበት ይሆናል።
5. ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት እና ፖሊስ ውስጣዊ ቅድመ ዝግጀት በማካሄድ በሀገር አቀፍ ደረጃ የቫይረሱን ስርጭት የመከላከል ሥራን ለማስፈጸም መዘጋጀት።
6. በተጠቃሚው ማኅበረሰብ ላይ ሕገ ወጥ የዋጋ ጭማሪን የሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚቀጥሉ ይሆናል።
7. መገናኛ ብዙሀን በትኩረት በየደረጃው ግንዛቤን የማሳደግ ሚና መጫወት ይጠበቅባቸዋል።
8. ብሔራዊ የመከላከያ ሠራዊት በድንበር አካባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ይገታል። ይህ እርምጃ ወደ ሀገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦችና አስፈላጊ መገልገያዎችን አይጨምርም።
በተጨማሪም ቫይረሱ በፍጥነት ቢዛመት ክልሎች ለይቶ ማቆያና ማከሚያ እንዲሁም የሕክምና ባለሙያዎቻቸውን እያዘጋጁ መሆኑን ገልጸዋል። አክለውም፣ ፌደራል መንግሥት የኮቪድ19ን የመከላከል ሥራን ለመሥራት 5 ቢሊየን ብር መመደቡን አስታውቀዋል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV