በዳባትና በጎንደር ከፋኖ ጋር መዋጋቱን የአማራ ክልል አመነ !


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


በዳባትና በጎንደር ከፋኖ ጋር መዋጋቱን የአማራ ክልል አመነ ! አብን በበኩሉ መንግስት ሕግ አስከብራለሁ ብሎ በሚንቀሳቀስበት ማንኛውም ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የዜጎች ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ እንዲሆን ጠይቋል።አስተያየት ሰጪዎች የአማራ ክልልን ድርጊት አውግዘው የኦሮሚያ ክልል በወለጋ ለተከሰተው ግጭት የእርቅ ኮሚቴ አቋቁሞ ችግሮቹን ለመፍታት ሲለሳለስ አዴፓ ብልጽግና በፋኖ ላይ ጦር መስበቁን ኮንነውታል።

በዳባትና በጎንደር ለተከሰተው ግጭት የአማራ ክልል ብልጽግና ፓርቲ የእምነት ክሕደት ቃሉን በመግለጫ ያስነበበ ሲሆን ፋኖን በሁለት በመክፈል አንዱን ሲወነጅል ሌላኛውን የሕዝብ የሰላም ጓድ ሲል አሞካሽቶታል። የአማራ ብልጽግና ፓርቲ መግለጫ በአሁኑ ወቅት እየተከሰተ ያለው ጉዳይ እጅግ አስቸጋሪ እየሆነ ነው፡፡ ፋኖ ቁሜለታለሁ ከሚለው አላማና ስነምግባር ውጭ በሆነ መንገድ በፋኖ ስም ያልተገቡ ስራዎች እየተሰሩ ነው፡፡ ብሎ በትላንቱ እለት ለሞትና ቁስለት የተዳረጉት የራሳችን የጸጥታ አካለት ናቸው፡፡ ጥቃቱ የደረሰውም የፖሊስ አባላቱ የህዝብን ሰላም ለማረጋገጥ ሲንቀሳቀሱ እንጅ፤ በፋኖ ስም እንደሚነግዱት አንዳንድ ግለሰቦች ለዝርፊያ ተሰማርተው አልነበረም፡፡ለህዝብ ሰላም ሲሉ አግባብ ያልሆነ መስዋትነት ከፈሉ፡፡ እጅግ በጣም ያማል ብሏል በመግለጫውብሏል፡፡
ፋኖ ቆሜለታለሁ ከሚለው የአማራን ህዝብ ሰላም የማስጠበቅ ስራ በተቃራኒ የቆሙትን አካለት ማስተካከል ካልተቻለው፤ ይሄን ጉዳይ ህዝብና መንግስት፤እንዲሁም ለሰላም የቆሙት የፋኖ አባላት በጋር የማስተካከል ኃላፊነት አለባቸው ብለን እናምናለን፡፡ ይሄን ማድረግ ካልተቻለ ግን፤ክልላችን የጉልበተኞች መፈንጫ ወደመሆን ያመራል፡፡ መንግስትና ህዝብ ደግሞ ይህ እንዲሆን በጭራሽ የሚፈቅዱ አይሆንም፡፡
አብን በፌስቡክ ገጹ ባሰራጨው ጽሁፍ እንዳለው ከትላንትናው ዕለት ጀምሮ በጎንደር ከተማ እና አካባቢው የፀጥታ ችግር እንዳለ ለማወቅ ችሏል። የችግሩ መነሻ እና ከዚህ ደረጃ የደረሰበትን ምክንያት ምን እንደሆነ በትኩረት በማጣራት ላይ እንገኛለን። ይህ በእንዲህ እንዳለ መንግስት ሕግ አስከብራለሁ ብሎ በሚንቀሳቀስበት ማንኛውም ሁኔታ ከፍተኛ የሆነ ጥንቃቄ እንዲያደርግ እና የዜጎች ሰብዓዊ መብት በጠበቀ መልኩ እንዲሆን አብን ይጠይቃል። ጉዳዩን በትኩረት በመከታተል ከሕዝባችን ጎን እንደምንቆም ለማሳሰብም እንወዳለን። #MinilikSalsawi