በሞጣ የድጋፍ ማሰባሰብ ዙሪያ ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ድረስ በ9 ባንኮች በተከፈቱት የገቢ ማሰባሰቢያ ሂሳቦች በጥሬ ገንዘብ 208,939,962.90 ብር (ሁለት መቶ ስምንት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከዘጠና ሳንቲም) በማሰባሰብ ከእቅድ በላይ ማሳከት ተችሏል

በሞጣ የድጋፍ ማሰባሰብ ዙሪያ
ከኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ምክር ቤት የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ

በአላህ ስም እጅግ በጣም አዛኝ፣ እጅግ ሩህሩህ በሆነው
• በአማራ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ምስራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ታህሳስ 10 ቀን 2012 በተፈፀመው የሽብር ጥቃት በከተማዋ የሚገኙ ጥንታዊና ታሪካዊ ቅርሶቸን፣ ቁርዓንና ኃይማኖታዊ መጽሐፍት የያዙ አራት መስጅዶች እና የመስጅድ ኢማሞች መኖሪያ ቤቶች መውደማቸው፤ ሙስሊሞች በአክሲዮን የገነቧቸው የተለያዩ የገበያ ማዕከላት፣ ሆቴሎች፣ ሱቆች እና መኖሪያ ቤቶች በውስጦቻቸው የነበሩ ንብረት እና በሚሊዮን የሚገመት ጥሬ ገንዘብ ሙሉ በሙሉ መዘረፋቸውና መቃጠላቸው ይታወሳል፡፡
• ከዚህ ጋር በተያያዘ የሽብር ጥቃቱ ሰለባዎች በግልጽ ለሚታይ ከፍተኛ ኢኮኖሚያዊ፣ ማህበራዊና የስነ ልቦና ችግሮች ተዳርገው እያለ ከፌዴራልም ሆነ ከክልሉ መንግስት እንዲሁም መንግስታዊ ካልሆኑ የተራድኦ ድርጅቶች ችግራቸውን ለመቅረፍ ድጋፍ ሊያደርግላቸውና ከጉናቸው ለመቆም የሞከረ አካል አልተገኘም።
• ስለዚህ ተጎጂዎች ወደ ከፋ ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ ችግር ውስጥ ከመግባታቸው በፊት ጠቅላይ ምክር ቤቱ ፍፁም ሰላማዊ በሆነ መንገድ ሁሉንም ኢትዮጵያዊያን አስተባብሮ የተቃጠሉ መስጅዶችን መልሶ ለመገንባትና ተጎጂዎችን ለማቋቋም ቅድሚያ በመስጠት የገቢ አሰባሳቢ ኮሚቴ አዋቅሮ በአፋጣኝ ወደ ሥራ መገባቱም የሚታወቅ ነው፡፡
• በዚህም መሰረት ጁማዓ ጥር 22/2012 በሀገር ውስጥ እና በተለያዩ የዓለም ሀገራት በይፋ የተጀመረው የገቢ ማሰባሰብ ንቅናቄ 200,000,000.00 ብር(ሁለት መቶ ሚሊዩን ብር) ለማሰባሰብ ታቅዶ እስከዛሬው እለት ድረስ በአገር ውስጥ በአይነት የተለገሰውን እና በአብዛኛው በውጭ አገር የተሰበሰበውን ገንዘብ ሳይጨምር ይህ መግለጫ እስከተሰጠበት ድረስ በ9 ባንኮች በተከፈቱት የገቢ ማሰባሰቢያ ሂሳቦች በጥሬ ገንዘብ 208,939,962.90 ብር (ሁለት መቶ ስምንት ሚሊዮን ዘጠኝ መቶ ሰላሳ ዘጠኝ ሺ ዘጠኝ መቶ ስልሳ ሁለት ብር ከዘጠና ሳንቲም) በማሰባሰብ ከእቅድ በላይ ማሳከት ተችሏል፤ አልሃምዱሊላህ።
• ይህ ከህፃን እስከ አዋቂ የተሳተፈበት ፍፁም ሰላማዊ እና አስተማሪ የሆነ በጎ ተግባር እንዲሳካ የበኩላችሁን የተወጣችሁ በአገር ውስጥና በውጪ የምትኖሩ ኢትዮጵያዊያን ከጥሬ ገንዘብ በተጨማሪ ግምቱ ከ750,000.00 ብር (ሰባት መቶ ሃምሳ ሺ ብር) በላይ የሚገመት የተለያዩ ከወርቅ፣ ከብርና ከነሐስ የተሰሩ ጌጣጌጦች የእጅ ሰዓትና የሞባይል ቀፎዎች ገቢ ተደርገዋል።
• ይህ የገንዘብ እና የአይነት መዋጮ የራሳቸው የሆኑ ብዙ ልዩ ታሪኮች ያዘሉ መሆናቸው እንደተጠበቀ ሆኖ
 ባለባቸው ኢኮኖሚያዊ ችግር ምክንያት በልመና የሚተዳደሩ ወገኖቻችን ለምነው ያገኙትን ገንዘብ ወገኖቻቸው እንደነሱ የሰው ፊት እንዳያዩ የለገሱትን፣
 እንደልብ መንቀሳቀስ የማይችሉ ወድማችን እንደእግር የሚገለገልበት ክራች ተሽጦ ለወገኖቹ እርዳታ እንዲውል ሰጥቶ በከፍተኛ ብር በጨረታ የተሸጠውን፣
 የወገኖቿ ኑሮ ወደነበረበት እንዲመለስ አዲስ ሙሽራ ሆና የጋብቻዋ ምልክት የሆነውን ቀለበቷን የሰደቀችውን፣
 ከ40 አመት በላይ የተቀመጠውን የቤተሰብ ቅርስ ሙዳይ ከነጌጣጌጡ የለገሱትን፤
 የቤተሰብ መተዳደሪያ ባጃጅ ለተቃጠለው ባጃጅ ምትክ ትሆን ዘንድ ያበረከተውን፣
 ለጁመዓ ሶላት የመጣበትን ሳይክል ስለመመለሻው ሳይጨነቅ ለወገኖቹ ጉዳት ማገገሚያ ሰጥቶ ማንም ሳያየው የሄደውን ተማሪ፣
 እንዲሁም በሀገራችን ደስታ እና ችግር ሁሌም ከፊት የሚቆሙት የሀገራቸን የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት ሸህ ሙሐመድ ሁሴን አላሙዲና ብዙ ባለሃብቶች ኃሳቡ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን ተወጥተዋል።
 ሌሎች በርካታ ልብ የሚነኩ የወገኔ ህመም ህመሜ ነው የሚል ተግባራዊ ምላሽ የተሰጠበት ሆኖ አልፏል።
• ይህ እንዲሳካ ከህዝበ ሙስሊሙ በተጨማሪ፡-
 አዲስ አበባን እና ድሬዳዋን ጨምሮ የሁሉም የክልል፣ የዞን እና የወረዳ እስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች፣
 የመስጅድ ኢማሞች፣ የመስጅድ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴዎች፣
 መሻኢኸሆችና ዱዓቶች፣
 የሞጣ አካባቢ ተወላጆች፣
 የመገናኛ ብዙሃን (ሚዲያዎች)፣
 ታዋቂ ሰዎችና የሀገር ሽማግሌዎች፣
 በየአካባቢው የሚገኙ የመስጂድ ወጣት ጀምዓዎች፣
 የክርስትና እምነት ተከታዮች ላሳዩት ወገናዊነት፣
 ባንኮች፤
 የፌዴራልና የክልል የፀጥታ አካላት
በዚህ በጎ ተግባር ላይ ለነበራችሁ ከፍተኛ አስተዋጽኦ ከልብ የመነጨ ምስጋናችንን እናቀርባለን፤ አላህ ጀዛአችሁን ይክፈላችሁ።
• ከዚህ በተጨማሪ በተለያዩ ሀገራት የምትገኙ ኢትዮጵያውያን በተከፈተው የዶላር አካውንት (ቁጥር 1137526/2/3401/0 ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ኦዳ ቅርንጫፍ Swift Code:- ORIRETEA) እስከ የካቲት 24/2012 (March 3/2020) ድረስ የሰበሰባችሁትን ገንዘብ ገቢ እንድታደርጉልን እናሳስባለን።
• ከዚህ በኋላ በማንኛውም ሁኔታ በመስጅድ ውስጥ በሞጣ ተጐጂዎችና በጠቅላይ ምክር ቤቱ ስም የሚደረግ የገቢ ማሰባሰብ እንቅስቃሴ የማይኖር መሆኑን እንገልፃለን።
• ከዚህ ቀጥሎ ጠ/ምክር ቤቱ ተጐጂዎችን ለማቋቋሚያ የተሰባሰበው ገንዘብ ለተጎጂዎች በአፋጣኝ መድረስ የሚችልበትን ሁኔታ የሚያመቻች ግብረ ሀይል አዋቅሮ ወደ ሥራ እንዲገባ በማድረግ ወገኖቻችን ወደ ሥራቸው በአጭር ጊዜ ተመልሰው እንደ ከዚህ ቀደሙ እራሳቸውን እና ሀገራቸውን እንዲጠቅሙ የሚቻለውን ሁሉ ያደርጋል።
• በተጨማሪም የፈረሱት መስጂዶች ተመልሰው እንዲገነቡና ማህበረሰብን የሚጠቅሙ ግልጋሎት የሚሰጡ ተቋማት ግንባታቸውን በተመለከተ በመስኩ ልምድ ያላቸውን ባለሞያዎችንና አማካሪ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት በአጭር ጊዜ ወደ ግንባታ እንዲገባ የምናደርግ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

በመጨረሻም ህዝበ ሙስሊሙ የመሪ ድርጅቱን ጥሪ ተቀብሎ ለዚህ በጐ ተግባር በአንድነት ለሰጠው ተግባራዊ ምላሽ በአላህ ስም ከፍ ያለ ምስጋናችንን እናቀርባለን፡፡ ህዝበ ሙስሊሙ በሞጣ ጉዳይ ያሳየውን መነቃቃትና ቀናነት ከመሪ ድርጅቱ ጋር በመሆን በቀጣይ ለሚኖረው ተልዕኮ ሁለንታናዊ ድጋፉን አጠናክሮ እንዲቀጠል ከወዲሁ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

አሏህ ሀገራችን ልጆቿ ተፍቃቅደው እና ተጋግዘው የልማትና ሰላም ተምሳሌት እንድትሆን ያግዘን፤ ያድርግል፤ አሚን!

አሏሁ አክበር!

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዩች ጠቅላይ ምክር ቤት
የካቲት 05/2012
አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ

Image may contain: text

Image may contain: text

Image may contain: text