ኢትዮጵያ በግለሰብ ነፃነት አጠባበቅ ከ54 የአፍሪካ ሀገራት 48ኛ ደረጃ መያዟን አንድ ሪፖርት አመለከተ፡፡


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


Ethio FM : በአፍሪካ ቀንድ ኢኮኖሚና ማህበራዊ ፖሊሲ ኢንስቲትዩት (HESPI) የተባለውን ተቋም የአፍሪካ የብልጽግና ጉዞ በሚል ባጠናው ጥናት ኢትዮጵያ በግለሰብ ነፃነት አጠባበቅ ረገድ ከ54 የአፍሪካ ሀገራት 48ኛ ደረጃ ላይ እንደምትገኝ አመልክቷል፡፡

ሪፖርቱ የግለሰብ ነፃነት ሲል ትኩረት የደረጉት ኤጀንሲዎችን ፤ የመሰብሰብና የመደራጀት ነፃነት ፤ የመናገርና መረጃ የማግኘት ነፃነት ፤ የህግ የበላይነትና ማህበራዊ መቻቻል ላይ ጥልቅ ጥናት በማድረግ መሆኑን ሪፖርቱ ተናግሯል፡፡

ከ54 የአፍሪካ ሀገራት ኬፕ ቬርዴ 1ኛ ደረጃ ስትይዝ ደቡብ አፍሪካ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ስትቀመጥ ሞሪሺየስ ሶስተኛ ደረጃ ይዛለች፡፡

ኤርትራ ከኢትዮጵያ በ8 ዝቅ ብላ መጨረሻውን ደረጃ ላይ ተቀምጣለች፡፡

በሌላ መልኩ በጠጥታና ደህንነት ከማስጠበቅ አኳያም ኢትዮጵያ ከ54 የአፍሪካ ሀገራት 40ኛ ደረጃን ይዛለች፡፡

በሪፖርቱ ከፀጥታና ደህንነት አኳያ ሲል ጦርነትና የእርስ በእርስ ግጭት ፤ ሽብርተኝነት ፤ ከፖለቲካ ጋር የተዛመደ ሽብርና ሁከት ፤ የዓመፅ ወንጀል ፤ ንብረት ላይ የሚሰነዘር ወንጀል ላይ ትኩረቱን አድርጓል፡፡

በዚህ ረገድ ኢትዮጵያ ከ54ቱ ሀገራት 40ኛ ደረጃ ስትይዝ ደቡብ ሱዳን መጨረሻ ላይ ተቀምጣለች፡፡ ቀዳሚ ደረጃ ላይ የተቀመጠችው ሳዎ ቶሜ ስትሆን ሞሪሺየስ እና ኮሞሮስ 2ኛ እና ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

እንደ ሪፖርቱ ገለፃ ከሆነ የምስራቅ አፍሪካ ሀገራት በነዚህ ጉዳዮች ላይ ደካማ አፈፃፀም እንዳላቸው ነው የሚያመለክተው፡፡