" /> ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ የውጭ ብድር ለመጀመሪያ ግዜ ቅናሽ አሳየ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ የውጭ ብድር ለመጀመሪያ ግዜ ቅናሽ አሳየ

ከፍተኛ ስጋት ውስጥ የገባው የኢትዮጵያ የውጭ ብድር ለመጀመሪያ ግዜ ቅናሽ አሳየ

በቅርቡ ይፋ የተደረገው የገንዘብ ሚኒስቴር የብድር ማሳወቂያ ሰነድ የኢትዮጵያ የውጭ ብድር በህሪውን በመቀየር ከማደግ ይልቅ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

የቀዳሚውን ግዜ ከ2012 በጀት አመት የመጀመሪያ እሩብ አመት ጋር በማነፃጸር ይፋ የተደረገው ሰነድ እንደሚያሳየው የአገሪቱ የውጭ ብድር ከ እሩብ ቢሊየን ዶላር በላይ ቅናሽ አሳይቷል፡፡
ለቅናሹም በመንግስት ዋስትና እና ካለ መንግስት ዋስትና የሚሰጡ ብድሮች መቀነስ አስተዋፅኦ እንዳለው ይፋ የተደረገው ሰነድ ያብራራል፡፡ ሆኖም የማእከላዊ መንግስት በመጠኑ ጭማሪ ማሳየቱን ነው መረጃው የሚያመላክተው፡፡

በበጀት አመቱ እሩብ አመት የአገሪቱ የውጭ ብድር ወደ 26.778 ቢሊየን ዶ/ር የወረደ ሲሆን በ2011 በጀት አመት መጨረሻ ይህ አሃዝ 27.029 ቢሊየን ዶላር ነበር፡፡
በመሆኑም የ251 ሚሊየን ዶላር ግድም ቅናሽ አሳይቷል፡፡ የገንዘብ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ሐጂ ኢብሳ ለቅናሹ አገሪቱ ካለፉት ሁለት አመታት ወዲህ ንግድ ተኮር ብድር ማቆሟን እደምክንያት አንስተዋል፡፡
ቀደም ብለው የተፈረሙ ብድሮች በሂደት በየግዜው የሚለቀቁ ናቸው ያሉት አቶ ሐጂ፤ አሁን ተለቀው በማለቃቸው እና ሌላ ንግድ ተኮር ብድር ባለመወሰዱ የመጣ ቅናሽ ነው ብለዋል፡፡ ይህ ቅናሽ የሚቀጥል እንደሆነ ይጠበቃል ብለዋል፡፡

source – https://www.capitalethiopia.com/featured/ethiopias-external-debt-drops/


የመረጃ ቲቪ አባል ይሁኑ - JOIN US