ፖሊስ ጫና አላደረገብንም ! – የኢንተር-ኮንቲኔንታል ሆቴል ስራ አስኪያጅ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

ከኢንተር-ኮንቲኔንታል ሆቴል እና ከእስክንድር ነጋ ተጨማሪ መረጃ!

“የሙዚቃ መሳርያ ያለበት የዩኒቨርሲቲ ምርቃት ፕሮግራም እንዲሁም የእነ እስክንድር ፕሮግራም አጠገብ ለአጠገብ ባሉ የአዳራሽ ክፍሎች ተገጣጥሞብን ነበር። የዩኒቨርሲቲው ፕሮግራም ቀደም ብሎ የተያዘ የነበረ ሲሆን ይሄኛው ግን በሁዋላ ላይ የተያዘ ነበር፣ እርግጥ ሁለቱንም አንድ ላይ መቀበል አልነበረብንም። ትናንት ማታ ደውለን ሌላ ቀን በፈለጋችሁበት ቀን አድርጉት፣ አለበለዛ የሙዚቃ መሳርያ ያለበት ፕሮግራም አጠገባችሁ ያለ አዳራሽ ውስጥ ስላለ ትረበሻላችሁ አልን። እነርሱ ግን አልተስማሙም። አሁንም በፈለጉበት ሌላ ቀን መጥተው ፕሮግራማቸውን ማካሄድ ይችላሉ። ፖሊስ ግን ጫናም አላደረገብንም።”— የኢንተር-ኮንቲኔንታል ሆቴል ስራ አስኪያጅ አቶ ወገኔ ማቴዎስ

“ሂልተን ሆቴልም፣ ራስ ሆቴልም፣ ኢትዮጵያ ሆቴልም ሲሉ የነበረው እኛ አልከለከልንም ነበር። አሁን ይሄ ለአራተኛ ግዜ መደገሙ ነው። ሆቴሎቹ ማለት ያለባቸውን ብለዋል። ከዚህ ውጪም አልጠበቅንም። ለእኛ ግን በውስጥ የሚነግሩን ሌላ ነገር ነው፣ ይሄ ከእኛ አቅም ውጪ ነው ይሉናል። ብዙ ግዜ ገንዘብ ከፍለን ከዛ ስለ ስብሰባችን በሚድያ ስናሳውቅ ነው ይሄ ክልከላ እየመጣ ያለው። ምክንያቱ ይሄ ከሆነ ገንዘብ ለምን ተቀበሉን? ብዙ ጥያቄዎች ሊነሱ ይችላሉ።”

የሁለቱንም ወገን ድምፅ ለማቅረብ ሞክሬአለሁ። የራሳችሁን ድምዳሜ መውሰድ የናንተ ድርሻ ይሆናል። Via Elias Meseret