ትረምፕ ግራ ገብቷቸዋል – የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

የአሜሪካ ኮንግረስ የውጭ ጉዳዮች ኮሚቴ ፕሬዝደንት ትረምፕ ትናንት በኖቤል ሽልማት ዙርያ የሰጡትን አስተያየት ተከትሎ “ትረምፕ ግራ ገብቷቸዋል” ብሏል!

ኮሚቴው በትዊተር ገፁ ላይ እንዳሰፈረው ጠ/ሚር አብይ አህመድ የኖቤል ሽልማትን የወሰዱት በአፍሪካ ቀንድ ሰላም ለማምጣት ላደረጉት ጥረት እንጂ በህዳሴ ግድብ ዙርያ ሲደረግ ለነበረው እና ሰሞኑን ካለ ውጤት ለተቋጨው ውይይት አልነበረም።

“ኖቤል ላልተሳኩ ስምምነቶች የሚሰጥ ቢሆን ፕሬዝደንቱ የመፅሀፍ መደርደርያ ሙሉ ሽልማት ይኖራቸው ነበር” ብሏል። Elias Meseret

Image may contain: text that says '13h House Foreign Affairs Committee Trump is confused. PM @AbiyAhmedAli was awarded the @NobelPrize for his efforts to bring peace to the Horn of Africa, not stalled negotiations about a new dam on the Nile. If they gave the Nobel for deals that didn't happen, the Pres. would have a shelf full of them. #Ethiopia'