መንግስት ምዕራብ ኦሮሚያ በሸማቂዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ በይፋ ተናግሯል


ኢትዮጵያን ካጋጠሟት እጅግ ውስብስብ ችግሮች ለማዳን የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን እና ገንቢ ትችቶችን የሚያቀርቡ ነፃ ሚዲያዎች ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ይታወቃል። ስለዚህም ኢትዮ360፣ መረጃ ቲቪ፣ አዲስ ድምጽ፣ ምንሊክ ቲቪ እና ሌሎችም የኢትዮጵያዊነት አጀንዳ የሚያራምዱ ሚዲያዎች በመተባበር ፕሮግራሞቻቸውን በሳተላይት ቲቪ ለኢትዮጵያ ህዝብ በማቅረብ ላይ ይገኛሉ። እነዚህ ሚዲያዎች የፈጠሩት ማህበር የሳተላይት ወጪውን መሸፈን እንዲያስችለው ይህን የጎፈንድሚ ፔጅ ከፍተናል → እዚህ ሊንክ ላይ ይጫኑ። ለትብብርዎ እናመሰግናለን።

VOA : መንግስት በሸማቂዎች ላይ እርምጃ እየወሰደ እንደሆነ በይፋ ተናግሯል! “ከሸማቂዎቹ ጋር የሚደረግ ድርድር የለም” – አቶ ታዬ ደንደአ ምዕራብ ኦሮሚያ ውስጥ በሚንቀሳቀሱ ሸማቂዎች ላይ መንግሥት ዕርምጃ እየወሰደ መሆኑን የኦሮምያ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ታዬ ደንደአ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ(VOA) ገልፀዋል። “ከሸማቂዎቹ ጋር የሚደረግ ድርድር የለም” ብለዋል የፓርቲው ቃል አቀባይ። የሸማቂዎቹ የምሥራቅና ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ መሪ “በእርምጃው እየተጎዳ ያለው ህዝቡ ነው” ብለዋል።