በከፍተኛ ትምህርት ደረጃ የሚሰጥ ትምህርት የጥራት ጉዳይ አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡

Sheger FMበከፍተኛ ትምህርት ደረጃ የሚሰጥ ትምህርት የጥራት ጉዳይ አነጋጋሪ እንደሆነ ቀጥሏል፡፡ ተቋማቱ በሚከተሉት ብልሹ አሰራር በተለይ በጤናው መስክ ስልጠና የሚሰጡቱ ኃላፊነታቸውና ተጠያቂነታቸው ሊታሰብበት የሚገባ ነው ተብሏል፡፡

– አንድ ስሙ ያልተጠቀሰ የትምህርት ተቋም ለፍቃድ ማግኛ በሚል ያቀረበው የቋሚ ቅጥር መምህር የትምህርት ማስረጃ በሕይወት የሌለ ሰው ሆኖ ተገኝቷል፡፡

– በተቋሙ ላይ የተወሰደው እርምጃን አስመልክቶ የተነገረ ነገር የለም፡፡

– ሐሰተኛ የእውቅና ፍቃድ እያሳተሙ ተማሪዎችን ተቀብለው የሚያስተምሩ ተቋማት በተደጋጋሚ ተገኝተዋል፡፡

– ያለ ምንም የተግባር ልምምድ የሚመረቁ የጤና ተማሪዎችም አሉ፤ ከብቃት ማነስ የተነሳም የሰው ሕይወት እያለፈ ነው ተብሏል፡፡ shegerFM


► መረጃ ፎረም - JOIN US