ለዜጎች ደህንነት መከላከያ ኦሮሞ ክልልን በሙሉ መቆጣጠር አለበት #ግርማካሳ


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


“ከኢህአዴግ የውህደት ሃሳብ ይልቅ የህወሓት ህብረብሄራዊ ፌደራሊዝም አስተሳሰብ አሸናፊነት እያገኘ ነው” ይላል ጃዋር መሐመድ፡፡ሕብረ ብሄራዊ ፌዴራሊዝም የሚሉት በሕወሃትና በኦነግ በሕዝቡ ላይ የተጫነ የጎሳ የዘር አወቃቀርን ነው፡፡

ሜዳ ላይ ያለውን ነባራዊ ሁኔታ ስንመለከት፣ ፍቃዱንና ፍላጎቱን በሌላው ላይ በኃይል ለመጫን የሚፈልገው፣ የጽንፈኞች ቡድን የበላይነቱን የያዘ ይመስላል፡፡ ብዙዎቻችን ተስፋ እንዳደረግነው ዉህደት የተባለው ነገር ሳይከሽፍ እንዳልቀረ ነው፡፡ “አልከሸፈም፣ እየተነጋገርንበት ነው፣ ከምርጫ በኋላ ይህናል ” የሚል ማዘናጊያ ንግግሮች እየሰማን ነው፡፡ የኦሮሞ ጽንፈኞች በአቶ ለማ መገርሳ በኩል የፈለጉትን እያገኙ ያለ፣ ዶ/ር አብይ አህመድም ወስኖ፣ ቆርጦ መምራት ያቃተው ይመስላል፡፡ ለሕዝብ የሚያቀርበው ነገር ስለሌለውም ኮስሜቲክ የሆኑ ፣ የተለመዱ የማዘናጊያ እንቅስቃሴዎችን በማድረግ ላይ ብቻ ነው የተጠመደው፡፡በአጭሩ አነጋገር የተሸነፈ፣ ለኦህዴድ ጽንፈኞች የተንበረከከ ነው የሚመስለው፡፡

በኦሮሞ ክልል በወለጋ፣ በአርሲ፣ በጉጂና በቦረና…ሕግና ስራዓት ያስጠብቃል ተብሎ የሚጠበቀው፣ የጦር ሃይሎች ጠቅላይ አዛዥ ዶ/ር አብይ አህመድ፣ ወንበዴዎችና አሸባሪዎች በመኪና ተጭነው በመምጣት፣ መሐል አዲስ አበባ እስኪያምሷት ድረስ ዝም ብሎ እያየ ነው፡፡ ምን እንደሚጠብቅም እግዜር ይወቀው፡፡

በጣም አዝናለሁ፡፡ ብዙዎቻችን እጅግ በጣም ከመጠን በላይ benefit of the doubt እየሰጠነው፣ እርሱ ላይ ላለመጨከን ወደ ኋላ ስንጎተት፣ በርሱ ላይ ተስፋችንን ሳናሟጥጥ ፣ የተለያዩ ሰበቦች እየሰጠን፣ ስራዉን ላለመስራቱ የተለያዩ ምክንያቶች በማቅረብ justify ስናደርግለት ቆይተናል፡፡ከሶስት፣ አራት ቀናት በፊት እንኳን ለዶ/ር አብይ ሁለተኛ እድል እንስጠው ብዬ ስከራከር ነበር፡፡

ግን ላለፉት ሁለት ቀናት የሆነው አይቼ፣ የዶ/ር አብይን ዝምታ በምንም መስፈርት justify ላደርገው፣ ልቀበለው አልችልም፡፡ በምንም አይነት ሁኔታ  !!!!!!!!

ቄሮ የሚባሉ ቡድኖች አሉ፡፡ እነዚህ ቡድኖች አንድ መረሳት የሌለበት ጉዳይ በኦህዴድ ሃላፊዎች የተደራጁ፣ የሚደገፉና ከመንግስት የኦህዴድ ሃላፊዎች ጋር በትብብር የሚሰሩ ናቸው፡፡ ሃላፊዎች በቀጥታ የማይሰሩትን ቁሻሻ ስራዎች የሚያሰሩት ባደራጇቸው ቄሮዎች ነው፡፡ በዶ/ር አብይ ፓርቲ ኦህዴድ የተደራጁና የሚደገፉ እነዚህ አሸባሪ ቄሮዎች ዛሬን ጨምሮ ላለፉት ሁለት ቀናት ብቻ  ከፈጸሙት እኩይ ተግባራት የሚከተሉት ይገኙበታል፡

 • ከደሴ ወደ አዲስ አበባ የሚመጣውን መንገድ በመዝጋት ህዝብ እንዳይመላለስ አድርገዋል፡፡ ሕዝብ ተጉላልቷል፡፡
 • ከሐረር ወደ አዲስ አበባ የሚወስደውን መንገድ ዘግተው ህዝብ እንዳይመላለስ አድርገዋል፡፡
 • በባስ የሚጓዙትን አስቁመው መንገደኞችን ዘርፈዋል፡፡ አዋክበዋል፡፡
 • በአዲስ አበባ ዙሪያ በአማርኛ የተጻፉ ማስታወቂያዎችንና ታፔላዎችን ነቃቅለዋል፣ መሬት ላይ ጥለዋል፡፡
 • በኩዬ ፈጬ መንገዶችን በመዝጋት ሕዝብ አሸብረዋል፡፡
 • በአቃቂ ክፍለ ከተማ የመንግስት መስሪያ ቤትን ሰብረው በመግባት የመንግስት ሰራተኞችን ደብድበዋል፡፡
 • በኢዜማ ስብሰባ ላይ፣  በሳሪስ፣ አሁንም እንደ ወንበዴ ስብሰባዉን በመረበሽ፣ የኢትዮጵያን ሰንደቅ መሬት ላይ በመጣል ሁከትን ፍጥረዋል፡፡
 • የአማራ ማህበር አባላት በአቃቂ ።ቃሊቲ ስብሰባ በሚያደርጉበት ጊዜ አዳራሹን በድንጋይ በመደብደብ፣ መስታወቶች ሰባብረዋል፤ ስብሰባዉንም እንዲጨናገፍ አድርገዋል፡፡
 • መኪናዎችን ፣ እያስቆሙ የኢትዮጵያ ሰንደቅ፣ የግእዝ ፊደላት፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶስክ አምነትን የሚያሳዩ ምልክቶች በመፋቅ መንገደኞችን አሸብረዋል፡፡
 • በአይሱዙ ተጭነው በአዲስ አበባ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ የመሬት ወራራ እያደረጉ፣ ለክሊኒክና ለተለያዩ የልማት ስራዎች በተመደቡ መሬቶች ላይ ምልክት በማድረግ ሕገ ወጥ ተግባራትን ፈጽመዋል፡፡
 • በአቃቂ ወረዳ ጽ/ቤት በመግባት የመንግስት ሰራተኞች ደብድብደ ብዙዎች ክፉኛ ቆስለው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡

እነዚህንና ሌሎች ሕገ ወጥ የሽብር ተግባራት ቄሮዎች ሲፈጽሙ የኦህዴድ ባለስልጣናት ሕግን የማስክበር ስራ ሲሰሩ፣ ሕዝብ ሲጠብቁ አልታዩም፡፡ ዜጎች በፍርሃትና በጭንቀት ውስጥ ነው የሚገኙት፡፡  በእጅግ በጣም ብዙ ሽብሮች በቄሮ እየተደረገ ነው፡፡ በአጭሩ አነጋገር ኦህዴዶችን የኦሮሞ ፖለቲከኞች ቄሮን በማሰማራት፣ ቄሮን ዝም ብሎ በመመልከት በተቀረው የኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ትልቅ ቀውስ እየፈጠሩ ነው፡፡ ለሕዝብ ከመቆም በሕዝብ ላይ እየመጡበት ነው፡፡

መፍትሄው ምንድን ነው ? መፍትሄው ቀላል ነው፡፡ የኦሮሞ ክልል መንግስት የሲቪል አስተዳደሩን ይዞ እንደቀጠለ፣ የክልሉን የሰላም ማስጠበቅ እንቅሳሴ ሙሉ ለሙሉ የፌዴራል መከላከያ መረከብ መቻል አለበት፡፡ በሚቀጥሉት ጥቂት ቀናት ውስጥ የኦሮሞ ክልል ፖሊስና ልዩ ፖሊስ መታገድ አለበት፡፡ የፌዴራል መከላከያ ሙሉ ለሙሉ ክልሉን እንዲቆጣጠርና ሰላምና መረጋጋት እንዲያሰፍን ፣ ዶ/ር አብይ አህመድ ትእዛዝ መስጠት መቻል አለበት፡፡ ከዚህ የባሰ ነእግር ሊመጣ አይቻልም፡፡ ያንን ማድረግ ካልቻለ  ግን አሸባሪዎች ለሚያደርጉት ሽብር 300% ተጠያቂ የሚሆነው እርሱ ነው፡፡ የሚፈሰው ደም በእጁ ነው፡፡

የመከላክያ ጦር ይግባ የምለው ሌሎች ማህበረሰባት ከቄሮ ለመጠበቅ ሳይሆን፣ ቄሮዎችን ለመጠበቅ ነው፡፡ ቄሮዎች እነርሱ ዱላ ይዘው ሽብር ሲፈጠሩ ሌላው ዝም ያላቸው ፈርቶ አይደለም፡፡ ትእግስተኛ፣ ጨዋና አርቆ አሳቢ ስለሆነ ነው፡፡ ሰላም ወዳድ ስለሆነ፡፡ ነገሮች የበለጠ እንዳይባባሱ፣ በንግግር ይፈታል በሚል ነው፡፡ እንጂ ገፍቶ ከመጣም እዚያኛውም  ቤት እሳት እንዳለ መታወቅ አለበት፡፡ ስለዚህ መከላከያ መግባቱ ለቄሮም ጥቅም የሚሰጥ ነው፡፡