" /> በኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ ለውዝግብ ፣ ለልዩነትና ለአለመግባባት ምክንያት ሲሆን ይስተዋላል። | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

በኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ ለውዝግብ ፣ ለልዩነትና ለአለመግባባት ምክንያት ሲሆን ይስተዋላል።

በኢትዮጵያ የሰንደቅ ዓላማ ፖለቲካ በተለይ በህዝቦቿ መካከል ለውዝግብ ፣ ለልዩነትና ለአለመግባባት ምክንያት ሲሆን ይስተዋላል። ከአገሪቱ ጥንታዊ ሥነ-መንግስት ምስረታ ጋር ተያይዞ ለረጅም ዓመታት ጥቅም ላይ እንደዋለ የሚነገርለት ልሙጡ አረንጓዴ ቢጫ ቀዩ ሰንደቅ አላማ ከሃገሪቱ አልፎ የመላው አፍሪቃ የነጻነትና የአንድነት ተምሳሌት፣ በመላው ዓለምም ጥቁር ነጭን ያሸነፈበት የድል ምልክት ሆኖ ሳለ በሃገር ውስጥ ግን ክብሩን እና የአባቶችን የተጋድሎ አደራ የዘነጋ ነው ሲሉ ብዙዎች ይስማማሉ። በተለይ ከባለፈው ዓመት ወዲህ በተለያዩ ሁነቶች ላይ በሕገ-መንግስት እውቅና ያለውም ሆነ ልሙጡ፣ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲ አርማዎች፣ የክልል ሰንደቅ ዓላማዎች ፣ ዋናውን እየተኩ ሲውለበለቡና አላስፈላጊ ፉክክር ሲታይ ይስተዋላል። ብዙዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን ሕገ-መንግስቱ መሻሻል እንዳለበትና፤ የሰንደቅ ዓላማውም ጉዳይ በዚያው የሚፈታ ይሆናል ነው።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV