" /> የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የተደራጁ ዘራፊዎች ስጋት ደቅነውብናል አሉ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የተደራጁ ዘራፊዎች ስጋት ደቅነውብናል አሉ

የኦሞ ኩራዝ ስኳር ፋብሪካዎች የሚሰሩ ሰራተኞች የህግ ያለህ እያሉ ነው! Elias Meseret

ሰራተኞቹ እንዳሳወቁኝ መንገድ ላይ በሚያጋጥማቸው የተደራጀ ዘረፋ ምክንያት በወታደር ታጅበው ለመንቀሳቀስ ተገደዋል። በባለፉት ጥቂት ሳምንታት ብቻ 2 ሾፌሮች የተገደሉ ሲሆን በዚህም ምክንያት የፋብሪካው ሰራተኞች በከፍተኛ ጭንቀት ውስጥ ይገኛሉ።

ኮርፖሬሽኑም ሆነ መንግሥት አስፈላጊውን ጥበቃ እንዲያደርጉ ግፊት ካልተደረገ አደጋ ላይ ነን ብለዋል። አክለውም የአደጋ አድራሾቹ ጥቃት በተለይ የስኳር ሰራተኞችን እና የመሥሪያ ቤት መኪኖች ላይ ያነጣጠረ ነው፣ በተለይ የደሞዝ እና የበአል ሰሞን።

አባሪ ደብዳቤውን ይመልከቱ።

No photo description available.


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV