በሐዋሳ ከተማ ህገወጥ የነዋሪነት መታወቂያ እደላ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ

በሐዋሳ ከተማ ህገወጥ የነዋሪነት መታወቂያ እደላ ተጠናክሮ ቀጥሏል።-ኢትዮ 360 ምንጮች

(ኢትዮ 360 ) በሐዋሳ ከተማ ህገወጥ የነዋሪነት መታወቂያ እደላ ተጠናክሮ መቀጠሉ ተሰማ።

ለኢትዮ 360 የደረሰው መረጃ እንደሚያመለክተው ህገወጥ መታወቂያው የሚሰጠው የከተማዋን ህዝብ ስብጥር ለማስተካከል ነው።

No photo description available.

በቁጥር ከፍተኛ እንደሆነ የሚገለጸው የመታወቂያ ደብተር በዋናነት የያዘው የሲዳማ ዞን ከተሞችን ስም ቢሆንም ማታወቂያው ላይ እንዲታተም የሚደረገው ማህተም ግን የሐዋሳ ከተማ ክፍለ ከተሞች መሆኑን ነው መረጃው ያረጋገጠው።

እንደዚህ አይነቱን ህገወጥ አሰራር ለመሸፈን በሚል በከተማዋና አካባቢዋ እየተከናወኑ ያሉት ኢሰብአዊ ድርጊቶችም ከመቼውም ጊዜ በላይ ተጠናክረው መቀጠላቸውም ታውቋል።

ከተማዋ በኮማንድ ፖስት ስር ናት ቢባልም ህገወጥ ድርጊቱንም ሆነ ህብረተሰቡ ላይ እየደረሰ ያለውን ኢሰብአዊ ድርጊት ሊከላከል አለመቻሉን ነው ምንጮቹ የሚገልጹት።

እንዲህ አይነቱ ኢሰብአዊ ድርጊት በእድሜ የገፉ አዛውንቶችና ደካማ ሰዎች ላይ ሳይቀር እንዲፈጸም የሚያደርጉት ደግሞ ከአንድ ብሔር የተውጣጡ የፖሊሶችና የፍትህ አካላት መሆናቸውም ታውቋል።

በከተማዋ ርካሽ የፖለቲካ አጀንዳን የሚያካሂዱትንና እንዲካሄድ የሚያደርጉትን አካላት የሚያስቆም ሌላ ሃይል ባለመኖሩ ሁኔታዎች ወደ አላስፈላጊ አቅጣጫ እየሄዱ መሆናቸውም ነው የተገለጸው።

በምስል ተደግፎ ለኢትዮ 360 የደረሰው ህገወጥ የመታወቂያ እደላ አሁንም ተጠናክሮ መቀጠሉን ነው ያመለከተው።