" /> ወጣቶች ከዘረኝነት አስተሳሰብና ስሜታዊነት በመውጣት ለአንድነታቸው በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

ወጣቶች ከዘረኝነት አስተሳሰብና ስሜታዊነት በመውጣት ለአንድነታቸው በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ

ኢዜአ – የኢትዮጵያ ብሄራዊ ክብሯና ሉዓላዊነቷ ለትውልድ እንዲሸጋገር በተለይ ወጣቶች ከዘረኝነት አስተሳሰብና ስሜታዊነት በመውጣት ለአንድነታቸው በጋራ መስራት እንዳለባቸው ተገለጸ።

Photo BBC Amharic

ለኢዜአ አስተያየታቸውን የሰጡ የተለያዩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዳሉት ኢትዮጵያዊነትን ለማጎልበት ዘላቂ ልማትና አስተማማኝ ሰላም መገንባት ይገባል።

አስተያየት ሰጭዎቹ እንዳሉት ጀግኖች አባቶና እናቶች ያቆዩትን ብሄራዊ አንድነትና አገራዊ ኩራት በተለያዩ የፖለቲካ አስተሳሰቦች ለመሸርሸር ሙከራ እየተደረገ ነው።

በደርግ ዘመን በሀገር መከላከያ ሰራዊት በተለያዩ ወታደራዊ ሃላፊነቶች ያገለገሉት ሻምበል ጥላሁን ተርፌሳ እንደሚሉት “ሰው አቅሙ የፈቀደውን ለሀገሩ አስተዋጽኦ ካደረገ” የሚያኮራ ተግባር ነው።

በሶማሌ ክልል መንገዶች ባለስልጣን ምክትል ስራ አስኪያጅ ኢንጂነር አብዱልቃድር በሽር እንዳሉትም ኢትዮጵያዊነት በራሱ የኩራት ምንጭ ነው ማለት ይቻላል።

“በየትኛውም አለም ላይ ስንቀሳቀስ በኢትዮጵያዊነቴ እኮራለው፤ ሰው የሚያውቀኝም በብሄሬ ሳይሆን በኢትዮጵያዊነቴ ነው” ብለዋል።

Image may contain: 5 people, people standing and outdoor

photo BBC Amharic

በመሆኑም ኢትዮጵያን ተደስተን የምንኖርባት፤ ለግል ጥቅማችን ሳይሆን ለጋራ እድገታችን የምንሰራባት ልዩነቶቻችንን በማክበር አንድነታችንን የምናጠብቅባት ለማድረግ ከታሪክ መማር አለብን ብለዋል።

ኢትዮጵያ የምትከተለው የብሄር ፖለቲካ ለወጣቶች የብሄር አጥር አበጅቶ በብሄር ብቻ እንዲያስቡ በማድረግ ሀገራዊ አንድነት እንዲሸረሸር እያደረገ ነው ብለዋል።

በመሆኑም በኢትዮጵያዊነቱ የሚኮራ ታሪክ አዋቂ ትውልድ ለመፍጠር ሥነ ምግባርን ከእውቀትና ከክህሎት ጋር አጣምሮ ማስተማር ይገባል ብለዋል።

ወጣቶች ያለፈው ትውልድ የፈፀመውን ጀግንነትና ያቆየውን ታሪክ እንደ አድዋ ያሉ የጥቁሮች ሁሉ ኩራት የሆነውን ታሪክ በቅጡ ማወቅ እንዳለባቸው ጠቁመዋል።

ቀደምት ጀግኖት አባቶቻችን “እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ” ተናበው ያቆዩልንን ሃገር በማህበራዊ ሚዲያ በሚሰራጭ የሃሰት መረጃ ልናፈርሳት አይገባም ብለዋል።


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV