ዘረኝነትን ተገን አድርጎ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ ኪሳራው የከፋ ነው። (ምንሊክ ሳልሳዊ )


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


(ምንሊክ ሳልሳዊ )ሁሉም ተጠቃሚ የሚሆንበትን የእኩልነትን ሃገር እንፈልጋለን። ሃገርህን፣ አንድነትህንና ሰላምህን ቅድሚያ ስጣቸው። የእኛ ብሔር አልተጠቀመም በሚል ዘረኝነትን ተገን አድርጎ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ ኪሳራው የከፋ ነው።መቻቻልም መከባበርን ካላስቀደም ውጤት አልባ ነው። በመንግስት በኩል ያለው የመዋቅር ፖሊሲ ካልተቀየረ የሕግ የበላይነት ካልሰፈነ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም።ንፁሃን ካለወንጀላቸው እስር ቤት መሆናቸውን እንዘንጋ።
 
ዘረኝነትን ተገን አድርጎ የፖለቲካ ትርፍ ለማግኘት የሚደረግ ሩጫ ኪሳራው የከፋ ነው ፤ ባለፉት 28 አመታት ሲሰበክ የነበረው የዘር ፖለቲካ ያመጣውን አደጋ በአይናችን እያየነው ነው ። ከዚህ ሳንማር ስለ ተጨማሪ የዘር ፖለቲካ ማራገብ ሌላ እልቂት መጋበዝ ስለሆነ ዘረኝነት ሊቆም ይገባል። ስለ መላው የሰው ልጆች መብት እና ነፃነት መከበር እንታገል። ዘረኝነት ጥንብ ነው። የዘር ፖለቲካን ማራመድ በሕዝብ ላይ እልቂትን መጋበዝ ነው። ዘረኝነት ይቁም !!!
 
ሰሞኑን የኑሮ መወደድን የዋጋ ግሽበትንና የገበያን ውሎ አስመልክቶ መንግስት ነጠላ ዘማዎቹን እየለቀቀ ነው። ኑሮ ቢወደድም ቢረክስም ሁሉም ነገር የሚኖረው ሃገር ስትኖር ነው። ቅድሚያ መንግስት በውስጡ ያሉትን መሰናክሎችና የሕዝብ ስጋት የሆኑ መዋቅሮቹን ሊያስወግድ ይገባል።መንግስት በራሱ ጉያ የታቀፈው እሳት ሲለበልበው ሕዝብ ላይ እያራገፈው የሕዝብ ሰላምን ማረጋገጥ አይቻልም።
 
በከፍተኛ ደረጃ የጥላቻ ቅስቀሳዎችን እያደረጉ ዘረኝነት የሚነዙ አካላትን ታቅፎ መንግስት የሕዝብን ሰላም ሊያረጋገጥ አይችልም። ሃገራችንን እያደቀቁ የሚገኙት በመንግስት መዋቅር ውስጥ ያሉ፣ መንግስት አቅፎ የያዛቸውና በማናለብኝነት የሚናገሩ ዘረኞች ናቸው።ይህ ደግሞ የመንግስት ፖሊሲ ድጋፍ ያለው በመሆኑ መፍትሔ ለማግኘት ተቸግረናል።
#MinilikSalsawi