“ተፈናቅለን የሚረዳንም አካል አጥተናል” – በባሌ ዞን ከ5000 በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች

VOA : በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ከአምስት ሺህ በላይ የሚሆኑ ሰዎች “ተፈናቅለን የሚረዳንም አካል አጥተናል” ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ቅሬታቸውን አሰምተዋል።የዞኑ የአደጋ ሥጋት ሥራ አመራር ፅሕፈት ቤት ደግሞ ሰዎቹ ተፈናቃይ አለመሆናቸውን ገልፆ ነገር ግን የምግብ እርዳታ እያደረሰላቸው መሆኑን ተናግሯል።የኦሮሚያ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ጉዳዩን የሚያጣራ ልዑክ ወደዞኑ መላኩን የክልሉ የመንግሥት ኮምዩኬሽንስ ቢሮ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጿል።

Image result for bale zone