በደብረ ብርሃን/ሸዋ ሕዝቡ በነቂስ አብን በጠራው ስብስበ ወጣ – ናኦሚን በጋሻው


መረጃ ቲቪ አባል በመሆን የሳተላይት ቲቪውን ቀጥታ ስርጭት፣ ወቅታዊ ዜናዎችን እና ትንተናዎችን፣ የመዝናኛ ፕሮግራሞችን፣ ስፖርት እና ሌሎችንም ዝግጅቶቻችንን በፍጥነት እና ጥራት ስልክዎ፣ ኮምፒዩተርዎ ወይም ቲቪዎ ላይ ማየት ይችላሉ። እዚህ ሊንክ ላይ በመጫን አባል ይሁኑ


ከተመሰረተ አንድ አመት የሆነው የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) ዛሬ እሁድ ሰኔ 9 ቀን 2011 ዓ.ም በሰሜን ሸዋ ዞን ዋና ከተማ በታሪካዊቷ ደብረብርሃኑ በጠራው ሕዝባዊ ስብሰባ ቁጥሩ እጅግ በጣም ከፍተኛ የሆነ ሕዝብ የተገኘ ሲሆን በስብሰባውም ከፍተኛ የድርጅቱ አመራሮች ለሕዝቡ ንግግር አድርገዋል።  ሕዝባዊ ስብሰባው በሁለት ቦታ የተደረገ ሲሆን፣ ከጠዋቱ 2:30 ጀምሮ በአፄ ዘርአ ያዕቆብ ስታዲየም፤ ከሰዓት በኋላ ከ 8:00 ጀምሮ ደግሞ በሲኒማ ደብረብርሃን አዳራሽ የተሳካ ሕዝባዊ ውይይት ተካሂዷል።

በደብረ ብርሃኑ በተደረገው ሕዝባዊ ስብሰባ በጣም ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር ያለው ህዝብ መገኘቱ፣ በአንድ በኩል የአብንን ድርጅታዊ ጥንካሬ የሚያሳይ ሲሆን በሌላ በኩል ክልሉን በሚመራው አዴፓ/ብአዴን ላይ ህዝቡ ተስፋ እየቆረጠ መምጣጡን የሚያመላክት መሆኑን ተንታኞች ይናገራሉ።

አብን ምንም እንኳን  በዘዉግ ስም የተደራጀ ቢሆንም፣ የፖለቲካው ፕሮግራሙና ማኒፌስቶ ግን ለዜግነት ፖለቲካ የቀረበ እንደሆነ የሚናገሩት ለአብን ቅርበት ያላቸው ተንታኞች፣ አብን በኢትዮጵያዊነት ላይ እንደማይደራደር፣ በአገሪቷ የዘር ፖለቲካ ለአገር ጉዳት ነው ብሎ እንደሚያምን፣ በኢትዮጵያ ሁሉም የዘዉግ ድርጅቶች ራሳቸውን ካከሰሙ፣ በአገር ደረጃ በዘር መደራጀት ከታገደ፣ አብን በደስታ ራሱን ለማከሰም ወደ አገር አቀፍ ድርጅትነት ለመቀየር ዝግጁ እንደሆነ የሚናገሩት ለአብን ቀርበት ያላቸው ተንታኞች፣ አብን የተደራጀው፣ የአማራን የበላይነት ለማስፈንና አማራን ልዩ ተጠቃሚ ለማድረግ ሳይሆን ፣ ሳይፈልግ ፣ ተገፍቶና፣ ላለፉት ሃያ ሰባት አመታት በተዘረጋው አማራ-ጠል ፖለቲካ አማራው ላይ ብዙ ፍ ስለደረሰ ራስን ለመከላከል ታስቦ እንደሆነ ይናገራሉ።