በአማራ ክልል የአመራር ለውጥ ሊደረግ መሆኑ ተሰማ

በአማራ ክልል የአመራር ለውጥ እንደሚደረግ ዶክተር አምባቸው መኮንን ገለጹ ( አብመድ)

ለሀገሪቱ ብሎም ለክልሉ ተጨባጭ ለውጥ ያመጣል ተብሎ የታመነበት የአመራር ለውጥ በአማራ ክልል እንደሚደረግ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ዶክተር አምባቸው መኮንን ገለጹ፡፡

በወረዳ፣ ዞንና ክልል ደረጃ እስከ 70 በመቶ የሚደርስ የአመራር መተካካት የተደረገባቸው ቦታዎች ቢኖሩም የመተካካት ሥራው በጥናት ያልተደገፈ እና በመረጃ ላይ የተመሠረተ ባለመሆኑ የተፈለገውን ውጤት አለመምጣንም ሲሉ ርዕሰ መስተዳድሩ ተናግረዋል፡፡

በተለያዩ የክልሉ አካባቢዎች በተደረገ ሕዝባዊ ውይይት የአመራር መተካካቱ ውጤታማ ያልሆኑባቸው አካባቢዎች መኖራቸውን መረዳት መቻሉን ዶክተር አምባቸው ገልጸዋል፡፡ በተለይ በቂ ልምድ የሌላቸው አመራሮች ከመኖራቸው ጋር በተያያዘ ሠራተኞችን በደንብ ወደ ሥራ ያለማሠማራት ውስንነት መኖሩንም ነው የገለጹት፡፡

ምንም እንኳን ሊዘገይ እንደሚችል ቢገመትም ባልተጠና መረጃ ላይ ተመሥርቶ አመራር ተክቶ መልሶ ከማፍረስ ይልቅ በቂ ጊዜ ወስዶ መሥራት ያስፈልጋል፡፡ የማይመጥኑ አመራሮችን በአዳዲስ የመተካት ሥራው ወደፊትም ተጠናክሮ እንደሚቀጥልም አስገንዝበዋል፡፡

 


► መረጃ ፎረም - JOIN US
► MEREJA TV YOUTUBE CHANNEL - SUBSCRIBE