በዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 ሰዎች ሞተዋል ተባለ

በምሥራቃዊ ዩጋንዳ በተከሰተ የመሬት ናዳ ቢያንስ 30 የሚሆኑ ሰዎች ሳይሞቱ እንዳልቀረ ባለሥልጣናት አስታውቀዋል። ባለሥልጣናቱ አክለውም የሟቾቹ ቁጥር ከተጠቀሰውም ሊበልጥ እንደሚችል ስጋታቸውን ገልፀዋል።

ላለፉት ጥቂት ቀናት በሀገሪቱ ከባድ ዝናብ ሲጥል የነበረ ሲሆን፣ ጎርፍ እና የመሬት ናዳ መከሰታቸውን የሚያሳዩ ሪፖርቶች መውጣታቸውን ተከትሎ መንግሥት ብሔራዊ የአደጋ ማስጠንቀቂያ አውጇል።