" /> የግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል | Mereja.com - Ethiopian Amharic News

የግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል

የአርበኞች ግንቦት 7 የባሕር ዳር ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል

አርበኞች ግንቦት 7 ለአንድነትና ለዴሞክራሲ ንቅናቄ በባሕር ዳር ከተማ በሀገሪቱ ወቅታዊ ሁኔታና ከሕዝብ ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት የጠራው ሕዝባዊ ውይይት ተቃውሞ ገጥሞታል፡፡

ወጣቶች ‹‹ግንቦት ሰባት የአማራ ጠላት ነው›› በማለት ውይይት በተጠራበት አዳራሽ አካባቢ ተቃውሞ እያሰሙ ነው፡፡

ንቅናቄው ለአዳራሽ ውይይቱ ተሳታፊዎችን በማስታወቂያና በመግቢያ ወረቀት መጋበዙን የውይይት ኮሚቴው አባል አቶ ዓለሙ ፈጠነ ተናግረዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን ወጣቶች ወደ አዳራሽ በመግባት የሰቀልናቸውን ጽሑፎች አውርደውብናል፣ የራሳቸውን ጽሑፍ በመስቀልም አውከውናል›› ብለዋል አቶ ዓለሙ፡፡

ተቃውሞ እያቀረቡ የሚገኙት ወጣቶች በበኩላቸው ‹‹ግንቦት 7 የአማራን ብሔርተኝት የሚያዳክም፣ በኢትዮጵያዊነት ስም አማራን እንዳይደራጅ የሚያሴር፣ ሀገሪቱ በብሔር ፖለቲካ መወጠሯን እያወቀ አማራ ብቻ ስለኢትዮጵያ እንዲያቀነቅን የሚወተውት ፀረ-አማራ ነው›› እያሉ ነው ሲል አብመድ ዘግቧል፡፡

Image may contain: one or more people, crowd and indoor

Image may contain: one or more people, people standing, crowd and outdoor

 


የመረጃ ቲቪ አባል በመሆን የስራችን ጥራት እንዲሻሻል ያግዙን። አባል ለመሆን እዚህ ላይ ይጫኑ።
JOIN Mereja TV