የሕወሓት ሳቦታጅ አንዱ ክፍል የመረጃ ቀውስ መፍጠር ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ውጥረት ከኢሕአዴግ የፖለቲካ ባሕሪይ አንጻር መለካት መጭውን ጊዜ ለማወቅ ይረዳል። ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው ፤ ለሕዝቡ የድንበር ውሳኔውን አጀንዳ ስለሰጠው ይህን ያሕል አይሰጋም ፤ አጃቢው አረና አጀንዳውን በሰላማዊ ሰልፍ ያደምቅለታል። በሰበር ዜናና በተባራሪ ዘገባዎች የመረጃ ቀውስ ተፈጥሮ የተቃዋሚዎች ትግል የእንቅልፍ ላይ የቅዠት መወራጨት አድርጎታል ።
ለኤርትራ ይሰጣሉ የተባሉት መሬቶች ሕጋዊ የውሳኔና የማስረከብ ፕሮሰሳቸው መስመሩን የተከተሉ አይደሉም ፤ ስለዚሕም ኤርትራ የሚፈለገውን ከመናገር ተቆጥባለች ፤ ሕጋዊ መስመሩ ኢሕአደግ ውሳኔው ለተመድ ቀጥታ ማሳወቅ ነበረበት ፤ ተመድም ለኤርትራ መንግስት ያስተላልፍና የኤርትራን መልስና መግለጫ ተከትሎ ሕጋዊ አግባቡ ይተረጎማል ። ወያኔ ግን ይህንን ሕጋዊ መስመር ካለመከተሉም በላይ የወሰነው ውሳኔ የሐገር ውስጡን ትኩሳት ለማብረድና በሰበር ዜናና በሰልፎች ሐገሩን ማመስ ይዟል። ወያኔ ኢሕአደግ በተከታይነት ሕዝቤ በውሳኔው ስላልተስማማ ተመልሼ ላጢነው የሚል ተመሳሳይ መግለጫዎችን ይለቃል ። #MinilikSalsawi