የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ሊያደርጉት ያቀዱት ሰልፍ መሰረዙ ተሰማ።

 

በሕወሓት ጥያቄ መሰረት የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ በኢትዮ ኤርትራ ድንበር ጉዳይ ላይ የወሰነውን ውሳኔ ለመቃወም የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች በአዲስ አበባ ሊያደርጉት ያቀዱት ሰልፍ መሰረዙ ተሰማ። የተሰረዘው በደሕንነት ስጋት ነው ብለዋል። የሕዝብን ደሕንነትና ሰላም ሲገፉ ኖረው ዛሬ ተገልብጦ ለነሱ ስጋት መሆኑ አስገራሚ የፖለቲካ ሂደት ነው።

የሕወሓት አባላትና ደጋፊዎች የኢሕአዴግ ምክር ቤት በባድመና በድንበር ከተሞች ላይ ያሳለፈውን ውሳኔ በመቃውም በመስቀል አደባባይ ሊያደርጉት ያቀዱትን ሰልፍ መሰረዙን የሕወሓት አፈቀላጤ የሆነው ሆርን አፍየርስ በድረ ገጹ ይፋ አድርጓል።

በሕወሓት ጥያቄ መሰረት የኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ በትግራይ ክልል የሚገኙ የድንበር ከተሞችን ለኤርትራ በ አልጀርሱ ስምምነት መሰረት አሳልፎ ለመስጠት መወሰኑ የሚታወስ ሲሆን ለኤርትራ ይሰጣሉ የተባሉትም ባድመ ኢሮብ ፆረና ዛላንበሳን ጨርሞ አስራ ሰባት ወረዳዎች ሲሆኑ ይህንን በመቃወም በተለያዩ የትግራይ ከተሞች ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል።