Blog Archives

ኢሕአዴግ የለውጥ እርምጃዎቹ ሕገመንግስታዊና ኢሕአዴጋዊ መሆናቸውን አረጋግጫለሁ ሲል መግለጫ አወጣ ።

ኢህአዴግ ምክር ቤት ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቀቀ ******************************* ከምስከረም 04-05/2011ዓ.ም ሲካሂድ የቆየው የኢህአዴግ ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን በማሳለፍ ተጠናቋል። ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመስከረም 4 እስከ 5 ቀን 2011 ዓ.ም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ ወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታና ለውጡን በብቃት የመምራት አስፈላጊነት ዙሪያ እና በ11ኛው ድርጅታዊ ጉባዔ ረቂቅ ሪፖርት ላይ ተወያይቷል፡፡ የኢህአዴግ ም/ቤት በመጋቢት ወር ባካሄደው ስብሰባ ያሳለፋቸውን ውሳኔዎች እና ያካሄደውን የአመራር ለውጥ ተከትሎ የተወሰዱ የለውጥ እርምጃዎች ህዝባዊ፣ ህገ-መንግስታዊ እና ኢህአዴጋዊ መሆናቸውን አረጋግጧል፡፡ በፖለቲካው መስክ ፖለቲካዊ መረጋጋት ለማምጣት ፣ የዴሞክራሲ ምህዳሩን ለማስፋት እና ሰብአዊ መብቶች ለማስከበር የተወሰዱ እርምጃዎች፣ በዲፕሎማሲው መስክ የተገኙ ውጤቶች በተለይም የኤርትራና የኢትዮጵያ ህዝቦችን ደም አቃብቶ የነበረው ጦርነት የፈጠረውን ለሁለት አስርተ ዓመታት የዘለቀው ፍጥጫ በመቅረፍ ወትሮውንም መኖር ይገባው ወደነበረ ቤተሰባዊነት በአጭር ጊዜ ውስጥ መመለስ የተቻለ መሆኑ ጉልህ ስፍራ የሚሰጠው መሆኑን እና ይህም ከጎረቤት ሀገራት ጋር የተሳሰረ ህልውና ያለን መሆኑን ግምት ውስጥ ያስገባ ሚናችንን በአግባቡ የምንወጣበት ዕድል እየተፈጠረ መምጣቱ፣በማህበራዊ መስክ በኢትዮጵያ ተዋህዶ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ እና በእስልምና እምነት ተከታዮች መካከል አንድነትን ለማጠናከር የተከናወኑ ተግባራት ዉጤት እንዳመጡ ገምግሟል፡፡ በተጨማሪም ሀገራዊ መግባባት ለማምጣት የተደረጉ ጥረቶች በተለይም በሀገራችን የተለያዩ የፖለቲካ አቋሞችን ይዞ ነገር ግን ከመጠፋፋት በመለስ ጎን ለጎን የሁሉም አለቃ ለሆነው ህዝብ በነፃነትና በሰላማዊ መንገድ ለመቅረብ የሚችሉበት የፖለቲካ ምህዳር ለመፍጠር የተጀመረው ጥረት በሀገራችን አዲስ ምዕራፍ ለመጀመር መሰረት
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሕአዴግ ውሳኔውን ተከትሎ የመጡ ለውጦችን በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል።

የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ መደበኛው ስብሰባውን የአመለካከት አንድነትን በሚያረጋግጥና የአመራሩን አቅም በሚገነባ መልኩ ማካሄዱን ቀጥሏል። መደበኛ ስብሰባውን ትናንት ነሃሴ 14/ 2010 ዓ.ም ማካሄድ የጀመረው የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ በጥልቅ ተሃድሶው የተላለፉ ውሳኔዎችና የተቀመጡ አቅጣጫዎችን አፈፃፀም እንዲሁም ውሳኔውን ተከትሎ የመጡ ለውጦችን በጥልቀት እየገመገመ ይገኛል። ጥልቅ ተሃድሶውን ተከትሎ እየመጡ ያሉ ሀገራዊ ለውጦች የሕዝቡን ፍላጎት በሚያሟላና ምልዓት ሕዝቡን ባሳተፈ መልኩ እየተፈፀሙ መሆናቸውን ማየቱን የኢሕአዴግ የሕዝብና ውጪ ግንኙነት ዘርፍ ሃላፊ ጓድ ሳዳት ነሻ ገልፀዋል። ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ይህን ሀገራዊ ለውጥ አጠናክሮ ለማስቀጠል የሚያስችል የአመለካከት አንድነት በድርጅቱ ውስጥ ሊያረጋግጥ በሚችልና የአመራሩን አቅም በሚገነባ መልኩ ውይይቱን ማካሄዱን ቀጥሏል።
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ዶ/ር አብይ በኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሕወሓትን ክፉኛ አስጠነቀቁ!

ዶ/ር አብይ በኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ስብሰባ ሕወሓትን ክፉኛ አስጠነቀቁ! ዛሬ በተጀመረው 36 አባላትን ብቻ በያዘው የኢሕአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ሕወሓትን ከዚህ በኋላ በአገራችን ላይ እየተሠራ ያለው አገርን የማተራመስ ድራማ ሊቀጥል አይገባውም ሲሉ አስጠነቅቀዋል። እየተሠራ ያለው አገርን የማተራመስ ድራማ በአስቸኳይ የማይቆም ከሆነ ሕዝብንና አገርን ለማዳን ሲባል መንግስት የማያዳግም እርምጃ ለመውሰድ የሚገደድ መሆኑን በማለት ጠንካራ ቃላቶችን በመጠቀም ተናግረዋል። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ በኢትዮ-ሱማሌ፣ በቤንሻንጉል ጉሙዝና በድሬዳዋ እንዲሁም ከአገር አልፎ በጎረቤት አገር በጅቡቲ በሚኖሩ ኢትዮጵያዊያን ላይ እየተደረገ ባለው ማፈናቀልና ጭፍጨፋ እነማን እንዳሉበት መንግስት ጠንቅቆ ያውቃል፣ አስፈላጊም ከሆነ በስም ጠርቶ መናገር ይቻላል። ሲሉ ቁጣ በተሞላበት ቃል የሕወሓትን ገመና አንድ በአንድ በስራ አስፈፃሚው ፊት ሲሰረግፉት አንድም የሕወሓት ባለስልጣናት ማስተባበያ ለመስጠት የደፈረ አልነበረም። ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ መንግስት እስካሁን የታገሰው ለሚፈሰው ደምና መፈናቀል ባለማሰብ ሳይሆን ይህን አስነዋሪ ስራ ተደራጅተው የሚሰሩ ሠዎች ከድርጊታቸው ተፀፅተው ይመለሳሉ በሚል ትዕግስት እንጅ ማንም ስለተፈራ አይደለም። እንደዚህ አስበው ከሆነ ተሳስተዋል፣ አሁንም ከድርጊታቸው ለመመለስ አልመሸባቸውም፤ ግን መንግስት ዜጎችን ለመጠበቅ ኃላፊነትና ግዴታ ስላለበት ሕግንና ስርዓትን የማስከበሩን ስራ ይሠራል ብለዋል። በዛሬዋ ቀን የኢህአዴግ ም/ ሊቀመንበሩና ም/ጠ/ሚነስትሩ አቶ ደመቀ መኮንንም ንግግር ተዋጦለት እንደዋለም እየተነገረለት ነው። አቶ ደመቀም ሲናገሩ አሁን እየታየ ያለውን ለውጥ ሕዝብ እንጂ ኢሕአዴግ አላመጣውም በመሆኑም ለውጡ ይቀለበሳል ብሎ የሚያስብ ካለ ያ ሰው ወቅቱን መረዳት የማይችል የአእምሮ በሽተኛ መሆን አለበት ሲሉ በሕወሓቶች ሰፈር አስደንጋጭ የሆነ
Tagged with:
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የተሃድሶ መድረኩ በኦህዴድ የስልጣን ጥማት በስርዓቱ እና በተቀመጠለት አቅጣጫ ባለመሄዱ ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ ነች ~ ዶ/ር ደ/ፅዮን ገ/ሚካኤል

“ሀገሪቱ አጣብቂኝ ውስጥ ነች” ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል በዛሬው ዕለት የትግራይ ምክትል ርእሰ መስተዳድር እና የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል ከትግራይ ከያንያን እና የሚድያ ባለሙያዎች ጋር በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ሲመክሩ ውለዋል። ዶክተር ደብረፅዮን ባቀረቡት የውይይት መነሻ ሀሳብ ላይ ሀገራችን አሁን ያለችበት ሁኔታ ቆም ብሎ ማሰብ የምያስፈልግበት ነው ብለዋል። ኢህአዴግ በተሃድሶ ግዜው ያስቀመጣቸው የለውጥ መንገዶች ከሞላ ጎደል መልካም ነገር የታየባቸው ቢሆኑም በጣም በርከት ያሉ ጉዳዮች ደግሞ በተፈለጉበት መንገድ አለመሄዳቸው አብራርተዋል። ዶክተሩ እንዳሉት “ለምሳሌ በእስር የነበሩ ወንጀለኞች የሚፈቱበት አቅጣጫ ያስቀመጥን ቢሆንም የፀጥታ ሀይል የገደለ ይፈታ ግን አላልንም። ምክንያቱም ህገ ወጥነት ነው” ብለዋል። በተሃድሶው ጊዜ ከአራቱ የኢህዴግ አባል ድርጅቶች ተሃድሶው በሚገባ እና ለትግል በሚጋብዝ መልኩ የመራው ህወሓት መሆኑ ገልፀው ግምገማው ደግመው እንድያዩት የተደረጉ ኦሆዴዶች እንደነበሩም ገልፀዋል። ዶክተር ደብረፅዮን በማብራርያቸው የጠቅላይ ሚኒስትር ሃይለማርያም ደሳለኝ ከስልጣን እለቃለሁ ማለታቸውን ተከትሎ በኦሆዴድ የታየ የሀላፊነት መቀያየር ሩጫ፤ ከፍተኛ የስልጣን ጥማትን የምያሳይ እና አሁን እየታየ ላለው ችግር መነሻ መሆኑም ገልፀዋል። በተለይም አሁን አሁን እየታዩ ያሉት የድጋፍ ሰለማዊ ሰልፎች ህገ መንግስቱ እና ህገ መንግስታዊ ስርዓቱ የሚፃረሩ መልእክቶች እየተላለፉበት ያሉ መሆኑም ገልፀዋል። ህገወጥ መልእክቶቹም መቆም እንዳለባቸው አሳስበዋል። ዶክተሩ በንግግራቸው በማነኛውም የአገራችን ህዝብ ያለ የመለወጥ እና የመልማት ፍላጎት በማነኛውም መልኩ መደናቀፍ የለበትም። እሳቸው እንዳሉት ከአማራም፣ ከኦሮሞም፣ ከደቡብም፣ ከሶማሌም፣ ከዐፋርም ወዘተ አብሮ መስራት የምያስችል ዲሞክራስያዊ ሀይል ስላለ ነገሮች የሚስተካከሉበት መንገድ ማፈላለግ ይገባል። ጥንቃዌም
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ይድረስ እስረኞች ለምን ተፈቱ ይፈታሉ ለምትሉ (እስረኞች ሲፈቱ አይነናችሁ ለሚቀላ)

ማሕሌት ፋንታሁን በእስር ላይ እያሉ በደረሰባቸው ድብደባ እና ተገቢ ህክምና ሳይሰጣቸው ህይወታቸው እዛው እስር ቤት ሆነው ላለፉት፤ ኢንጅነር ተስፋሁን ጨመዳ ፣ ኒሞና ጥላሁን፣ ሙባረክ ይመር፣አየለ በየነ፣ አብደታ ኦላንሳ እና ሌሎችም በእስር እያሉ ሳይገባ ህይወታቸው ላለፉ እስረኞች ቤተሰቦች/ወዳጅ ዘመዶች የእስረኞች መፈታት ምንድነው? ምርመራ በሚል ሰበብ አካላቸው ለጎደለባቸው ለእነ አበበ ካሴ፣ ከፍያለው ተፈራ፣ አስቻለው ደሴ፣ መቶ አለቃ ጌታቸው መኮንን እና ሌሎች በርካቶች ከእስር መፈታት ምንድነው? ተፈቱ የተባሉት እስረኞች ከሚደርስባቸው አካላዊ እና አእምሯዊ ጉዳት በተጨማሪ ህገ መንግስቱ የሚፈቅድላቸውን ከቤተሰብ የመገናኘት እና ክሳቸውን የመከላከል መብታቸውን በሚጋፋ መልኩ (አብዛኛዎቹ ከቤተሰቦቻቸው ተገናኝቶ ጠበቃ ለማቆም እና መከላከያቸውን ለማሰባሰብ ቤተሰቦቻቸውን ለማግኘት ስለማይችሉ ሳይከላከሉ ነው የሚፈረድባቸው)። ከመኖሪያ ቤታቸው እና ቤተሰቦቻቸው በርካታ ኪሜ ርቀት ላይ ነው ክስ የተመሰረተባቸው፤ ታስረውም እንዲቀመጡ የተደረገው። በሁለት እና ሶስት አመት ፍርድ ቤት መመላለስ ብቻ ፍርድ ማግኘት እድለኝነት ነው። ፍርድ ቤቶች የሚሰጣቸው ቀጠሮ በጣም ረጃጅም ነው። ሌላም ብዙ ፍትህ የማግኘት መብታቸውን የሚፃረሩ ዘርዝሬ የማልጨርሳቸው በደሎች ደርሶባቸዋል። እየደረሰባቸውም ነው። ይህን ሁሉ አሳልፈው ለምን ተፈቱ ይባልልኛል። ከተፈቱ በኋላ ወደ ስራቸው ለመመለስ ፣ ጤናቸውን ለመመለስ (መመለስ የሚቻለውን)፣ እና ሌሎች የሚገጥሟቸው ማህበራዊ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፈተናዎች እንዳሉ ሆነው ማለት ነው። የእስረኞቹ መፈታት እስረኛ የነበሩ ቤተሰቦቻቸውን በሞት ላጡት ምንም ነው። በህይወት ለወጡትም ቢሆን መፈታታቸው የደረሰባቸውን በደል፣ ያሳለፉትን ስቃይ፣ ያጡትን አካል … አይመልስላቸውም። የቤተሰቦቻቸውን አንግልት እና ስቃይም አይመልስም። ታስረን ስንፈታ ፤ እስረኞች
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የሕወሓት መግለጫ አንድምታዎች፤ (ዳንኤል ኪባሞ)

የሕወሓት መግለጫ አንድምታዎች፤ (ዳንኤል ኪባሞ) ሕዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓት) ትናንትና ያወጣው መግለጫ በርካታ አጀንዳዎችን የሚዳስስ ነው፡፡ ከመግለጫው በግልጽ መረዳት የሚቻለው የሕወሓት አመራር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የለውጥ ጎዳና ላይ ከፍተኛ ቅሬታ እንዳለው፤ ይልቁንም ሕወሓት ለውጡ ደረሰበትን ደረጃ መረዳት ተስኖት ቆሞ መቅረቱን ነው፡፡ ኢሕአዴግ የሚመራበት አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊና ልማታዊ መስመር አደጋ ላይ እንደወደቀ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የአልጀርሱን ውሳኔ ተቀብሎ ባድመን ለመመለስ መስማማቱ ለሕዝብ የተገለፀበት መንገድ ትክክል አለመሆኑ፣ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች የሚሾሙበት መንገድ ከተለመደው አሠራር ያፈነገጠ መሆኑ እና የቀድሞ የድርጅቱ መሪዎች ሊከበሩ እንደሚገባ ወዘተ. ተመልክቷል፤ በመግለጫው፡፡ መግለጫውን ከለውጡና ከአገራችን የወደፊት እጣ ፈንታ አንጻር ካየነው ዕድልም አደጋም ያዘለ ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሕወሓት በበላይነት ሲመራው የቆየው ሥርዓት በአገርና በሕዝብ ላይ ምን ያህል መከራ እንዳመጣ መግልጽ አያስፈልግም፤ በግልጽ ስለሚታወቅና እየኖርነው ስለሆነ፡፡ ስለሆነም “አገራችን ከዚህ አስከፊ የብሉይ ዘመን ጭቆና እየተላቀቀች ነው፤ ለዚህም ዶ/ር ዐቢይና ጓዶቻቸው ከፍተኛ ሚና እየተጫወቱ ነው፤” ብሎ የሚያምነው ብዙሃኑ ኢትዮጵያዊ ዜጋ የተጀመረው በጎ ጅምር በሕወሓት መሪዎች እንዳይቀለበስ በዶ/ር ዐቢይ ከሚመራው አዲሱ የለውጥ ኀይል ጎን ይሰለፋል፡፡ በዚህ ምክንያት አዲሱ የለውጥ ኀይል በሕዝብ ሲደገፍና አቅሙ ሲፈረጥም፣ ከዚህ በተቃራኒው ለውጥን ተጻርሮ የቆመው ሕወሓት ይነጠልና ይዳከማል፤ እንቅፋትነቱ ያቆማል፡፡ ይህ ለጠቅላይ ሚኒስትሩም ሆነ እሳቸው ለጀመሩት የለውጥ ሒደት ትልቅ ዕድል ነው፡፡ መግለጫው አደጋም ያዘለ ነው ሊባል የሚችለው ደግሞ፣ ሕወሓት ለውጡ የደረሰበትን ደረጃና የብዙሃኑን ኢትዮጵያዊ ፍላጎትና ቁርጠኝነት መረዳት አቅቶት፣ በለውጥ እንቅፋትነቱ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው

የሕወሓት ሳቦታጅ አንዱ ክፍል የመረጃ ቀውስ መፍጠር ነው፤ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የፖለቲካና የኢኮኖሚ ውጥረት ከኢሕአዴግ የፖለቲካ ባሕሪይ አንጻር መለካት መጭውን ጊዜ ለማወቅ ይረዳል። ሕወሓት ምስጢራዊ ስብሰባ ይዞ በጭንቀት ያምጣል ፤ ትግራይ በሰላማዊ ሰልፎች እየተጥለቀለቀች ነው ፤ ለሕዝቡ የድንበር ውሳኔውን አጀንዳ ስለሰጠው ይህን ያሕል አይሰጋም ፤ አጃቢው አረና አጀንዳውን በሰላማዊ ሰልፍ ያደምቅለታል። በሰበር ዜናና በተባራሪ ዘገባዎች የመረጃ ቀውስ ተፈጥሮ የተቃዋሚዎች ትግል የእንቅልፍ ላይ የቅዠት መወራጨት አድርጎታል ። ለኤርትራ ይሰጣሉ የተባሉት መሬቶች ሕጋዊ የውሳኔና የማስረከብ ፕሮሰሳቸው መስመሩን የተከተሉ አይደሉም ፤ ስለዚሕም ኤርትራ የሚፈለገውን ከመናገር ተቆጥባለች ፤ ሕጋዊ መስመሩ ኢሕአደግ ውሳኔው ለተመድ ቀጥታ ማሳወቅ ነበረበት ፤ ተመድም ለኤርትራ መንግስት ያስተላልፍና የኤርትራን መልስና መግለጫ ተከትሎ ሕጋዊ አግባቡ ይተረጎማል ። ወያኔ ግን ይህንን ሕጋዊ መስመር ካለመከተሉም በላይ የወሰነው ውሳኔ የሐገር ውስጡን ትኩሳት ለማብረድና በሰበር ዜናና በሰልፎች ሐገሩን ማመስ ይዟል። ወያኔ ኢሕአደግ በተከታይነት ሕዝቤ በውሳኔው ስላልተስማማ ተመልሼ ላጢነው የሚል ተመሳሳይ መግለጫዎችን ይለቃል ። #MinilikSalsawi
Tagged with: , , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ ኤኮኖሚ ሊብራላይዜሸን እና ኢትዮ- ኤርትራ ደንበር ውሣኔ (ግርማ ሰይፉ ማሩ)

የኢህአዴግ ሥራ አስፈፃሚ/መንግስት ያልተጠበቀ ውሣኔዎችን አስተላልፏል፡፡ በተቃዋሚ ጎራ ደግሞ ግር የሚያሰኙ አስተያየቶች እየተደመጡ ነው፡፡ እነዚህ አስተያየቶች የኢትዮጵያ ፖለቲካ ግራ የገባው መሆኑ ገላጩ ናቸው፡፡ ፖለቲከኞቹ ግራ ተጋብተው ግራ የሚያጋቡ መሆናቸውን ያሳብቃል፡፡ እኔም በአጋፋሪነት የምሳተፍበት የተቃውሞ ጎራ ምን እንደሚፈልግ ግራ ግብት ነው የሚለኝ፡፡ ለዚህ መነሻ የሆነኝ ደግሞ ትላንት በሰበር የሰማነው ወሳኝ የሆኑ የኤኮኖሚ እርምጃዎች እና የኢትዮ- ኤርትር “ሠላምም ጦርነትም የለም” አሰብሎ ላለፉት አሰራ ሰምንት ዓመታት ቅርቃር ውስጥ የከተቱን ጉዳዮች ናቸው፡፡ ሁለቱም ላይ በአጭር በአጭሩ የግል ምልከታዬን ላጋራ፤ለምልከታዬ መሰረት የሆነኝ የወዳጄ ሙሉነህ እዮኤል ፌስ ቡክ ፖስት ነው፡፡ የኤኮኖሚ ሊብራላይዤሽን ውሣኔዎች ይህ ውሣኔ በተቃዋሚ ጎራ ያለን ሰዎች በሙሉ መንግሰት እራሱን ከተመረጡ ስትራቴጂክ መስኮች ውጭ ከንግድ ተግባር እንዲወጣ ስንወተውት ነበር፡፡ ይህ ውትወታ በአንድም በሌላ መልኩ ሳይደመጥ ቆይቶ ዛሬ በሆነ አስገዳጅ ሁኔታ ለመተግበር ሲታሰብ አሰቂኝ ጥያቄዎች እየተነሱ ነው፡፡ ከተነሱት ጥያቄዎች መካከልም የኢኮኖሚ አማካሪዎች እነማን ናቸው? ይህን የፖሊሲ ምክር የሰጠው ዓለም ባንክ? የዓለም የገንዘብ ተቋም? ወይስ ቶኒ ቢሊየር? የሚሉት ይገኙበታል፡፡ የማን ምክር ሲሆን ነው ይህን ወሣኔ ጥሩ ነው ለማለት የምንዘጋጀው? እነዚህ ሰዎች በመቃብራቸን ላይ ያሉት ጉዳይ ለመቀየር መሲ መጥቶባቸዋል፡፡ መቃብረ ከመውረዳቸው በፊት ሃሣብ ከቀየሩ መቃብር ካልወረዳችሁ አናምናችሁ ማለት ምን እንዳመጣው አይገባኝ፡፡ ለማንኛውም መቃብር አፋፍ ላይ ደርሰው፤ መቃብር ከመግባት ፖሊስ ማሻሻል ይሻለናል ማለታቸው ዘገየ ያስብል እንደሆነ እንጂ ለምን የሚያስብል አይመስለኝም፡፡ በእኔ እምነት ትግል የማደርገው ኢህአዴግን መቃብር ለማውረድ አይደለም፡፡
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሕአዴግ የአልጀርሱን ስምምነት በሙሉ ድምጽ አጸደቀ ፤ የባድመንና የዛላንበዛን ቡሬን ቦታዎች ለኤርትራ ለመስጠት ተስማማ። (መግለጫውን ይዘናል።)

ኢሕአዴግ የአልጀርሱን ስምምነት በሙሉ ድምጽ አጸደቀ ፤ የባድመንና የዛላንበዛን ቡሬን ቦታዎች ለኤርትራ ለመስጠት ተስማማ። ሕወሃት ከገባበት አጣብቂኝ ለመውጣት በመቀሌ ወስኖ የመጣውን አጀንዳ በኢሕአዴግ ስራ አስፈጻሚ አጸድቆታል። መግለጫም ወጥቷል። ከመቶ ሃምሳ ሺህ በላይ ወጣቶች የሞቱበትና ለኢትዮጵያ ተወስኗል ተብሎ የተነገረለት ባድመና የድንበር አከባቢዎች በሙሉ ለኤርትራ ይመለሳሉ። መግለጫውን ይዘናል። ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ (የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በማስመልከት የተላለፈ ጥሪ) የኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የኢትዮ-ኤርትራ ወቅታዊ ሁኔታን በጥልቀት በመገምገም በኢትዮጵያና ኤርትራ መካከል ተፈጥሮ የቆየው አለመግባባት እንዲያበቃና በሁለቱ ወንድማማች ህዝቦች መካከል ዘላቂ ሰላም እንዲፈጠር የሚከተለዉን ጥሪ አስተላልፏል። ለኢትዮጵያችን እድገትና ለሕዝቦች ተጠቃሚነት ሰላም ከምንም በላይ ትልቅ ዋጋ አለው፡፡ ሰላም የሁሉም ነገር መሰረት ነው፡፡ ከግለሰብ የወደፊት የማደግና መለወጥ ህልም ጀምሮ እስከ ሀገር ድረስ ሰላም ከደፈረሰ የቱንም አይነት የልማትና የዲሞክራሲ አላማዎችን ማሳካት አይቻልም፡፡ በኢትዮጵያና በኤርትራ መሃከል ከ1990 ዓ.ም ጀምሮ የተከሰተውን ጦርነት በአፍሪካ ከተከሰቱ የድንበር ጦርነቶች ሁሉ ደም አፋሳሹ ሲሆን፣ ከሁለቱም ወገን በርካታ ሺህ የሰው ሕይወት ሊጠፋ ችሏል፡፡ ጦርነቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን ከኤርትራና ከኢትዮጵያ የድንበር አካባቢ የመኖሪያ ቀዬ አፈናቅሏል፡፡ በሁለቱ ሀገራት መሃከል የተደረገው ጦርነት በሁለቱም ሃገራት ያሉ ቤተሰቦችን አፍርሷል፣ በድንበር አቅራቢያ የሚኖሩ ዜጎች ሁሌም ያለመረጋጋትና የስጋት ስነ-ልቦና ሰለባ አድርጓቸዋል፡፡ በድንበር አካባቢ በንግድ የሚተዳደሩ ሰዎች ላይ ተፅዕኖ ፈጥሯል፡፡ በድምሩ ላለፉት 20 አመታት በሁለቱም ሀገራት ህዝቦች ላይ መጠነ ሰፊ ኢኮኖሚያዊ፣ ማኅበራዊና ፖለቲካዊ ቀውስ ፈጥሯል፡፡ በመሆኑም የሁለቱ ሀገራት የወደፊት ግንኙነት
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ከቆመበት ቀጥሏል ፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገመገማሉ።

ሰላሳ ስድስቱ የኢሕአዴግ የስራ አስፈጻሚዎች መደበኛ ስብሰባ ከቆመበት ቀጥሏል፤ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይገመገማሉ። (ምንሊክ ሳልሳዊ) ስብሰባው ዶክተር አብይ አህመድ የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ስልጣን ከያዙ በኋላ የመጀመሪያ መደበኛ የፓርቲ ስብሰባ ነው። ፓርላማው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን የሰረዘው ሲሆን ከዚሁ ጋር ተያይዞ ቀጣዮ ኮማንድ ፖስቱ ስራው ምን መሆን እንዳለበት ውይይት ይደረጋል ከዚህም ጋር ተያይዞ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከተሾሙ በኋላ የነበራቸው የስራ ሂደት ይገመገማል ። ኢሕአዴግ አሁን እየታየ ባለው የለውጥ ጅማሮ እየተናጠ መሆኑን ምንጮቹ የጠቆሙ ሲሆን በቀጣይነት ወይ ይፈርሳል አሊያም የድምጹን ሂደት ያስተካክልና የሕወሃትን የበታችነት ያረጋግጣል ተብሎ ይጠበቃል። አንዳንዶች ኢሕአዴግን እንደ አጭበርባሪና አዘናጊ ድርጅት የሚያዩ ሲሆን በርካቶች ግን ለውጥ በመኖሩ ሂደት ላይ ይስማማሉ። የሕወሃት ሊቀመንበር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ የሚካሔደውን ለውጥ ያላስደሰታቸው ሲሆን በተለይ የእስረኞች መፈታትና ዶክተር አብይ በአምቦ ተገኝተው ባደረጉት ንግ ግር ደስተኛ አለመሆናቸውን ከመግለጻቸውም በላይ በማሕበራዊ ድረ ገጽ ላይ ካድሬዎቻቸውን በማሰማራት የተቃውሞ ዘመቻ እያካሄዱ ነው። ዶክተር አብይ አምቦ ላይ በቄሮ ትግል ስልጣን ላይ ወጥተናል እናመሰግናለን ማለታቸው እስካሁን በሕወሓቶች እየታሙበት ነው። የኢሕአዴግ ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነት መሰረት የአብይ ደጋፊ የሚባሉት ለማ ፣ ደመቀና ገዱ ከፍተኛ የሆነ ግምገማ ይጠብቃቸዋል። ሕወሓቶች አብይ ለኢሕአዴግ ሊቀመንበርነት የተመረጠበት መንገድ አብዮታዊ ዲሞክራሲን የተከተለ አይደለም በማለት ይተቻሉ። አለመተማመን እንደ ወረርሽኝ በሽታ በኢሕአዴግ ውስጥ ተስፋፍቷል። ሕወሓቶች ኦሕዴድን አብዮታዊ ዲሞክራሲንና ዲሞክራሲያዊ ማእከላዊነትን የካደ ለይስሙላ ኢሕ አዴግ ውስጥ የተሰነቀረ የከሐዲዎች ስብስብ ሲሉ ይወርፉታል። በስራ አስፈጻሚው ስብሰባ ላይ ጡረታ የወጡ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ኢሕአዴግ የፖለቲካ የበላይነቱን የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲቆጣጠሩት በጋራ እቅድ እየነደፈ ነው።

ኢሕአዴግ የፖለቲካ የበላይነቱን የኦሮሞ ድርጅቶች እንዲቆጣጠሩት በጋራ እቅድ እየነደፈ ነው። የሕወሃት የበላይነት በኢኮኖሚ መፈርጠሙን ያረጋገጠው ኢሕአዴግ በኦሕዴድ እና በኦነግ የፖለቲካ የበላይነት ሃገሪቷን ለማስተዳደር ማቀዱን ምንጮች ይጠቁማሉ። የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ መሾምን ተከትሎ በፈጠነ መልኩ ከኦነግ ሰዎች ጋር ድርድር መካሔዱ ኢሕአዴግ ባቀደው ቀጣይ የ አገዛዝ መስመር ላይ የኦሮሞ ፓርቲዎች አድራጊና ፈጣሪ ሆነው በፖለቲካ የበላይነት እንዲወጡ የሚደረግ ሒደት መስተካከሉና በውይይት ቀጣይ ስራዎች ሊስሩ እንደሆነ ተጠቁሟል። ለሕዝቡ እርባና የለሽ ነገር ከመፍጠር ውጪ ምንም ለውጥ አያመጡም። ኢሕአዴግ ከስሩ ተነቅሎ ካልተወገደ በቀር በኢትዮጵያው ውስጥ ታሪክ ላለፉት አመታቶች ራሱን እየደገመ ኢሕ አዴግ አፈር ልሶ እየተነሳ እያየን ነው። ለሕዝብ ጥቅም መቆም ማለት የስርዓት ለውጥ እንዲመጣ ከድርድር ጀምሮ መታገል ነው። ፖለቲካው በ አጭበርባሪነትና እና በሽፍጥ በሴራና በተንኮል የተሞላ እስከሆነ ድረስ የኢሕ አዴግን እድሜ ከማስረዘም ውጪ ምንም አይፈይድም። ሕዝባዊ መንግስት ለመትከል መጀመሪያ የሽጝር መንግስት ማቆም ያስፈልጋል። ከዚህ ውስጥ እንደ ኦፌኮና ሌሎች የኦሮሞ ድርጅቶች የተወሰነ ድርሻ እንዲኖራቸው ቢደረግም በበላይነት የሚመሩት ግን ኦሕዴድና ኦነግ ናቸው። ኢነግ ስሙን ቀይሮ ኦዴፍ ቢልም ምንም አይነት ከህወሃት የተለየ አስተሳሰብ የሌላቸው እና ከሕወሓት ጋር ያደጉ አዛውንቶች ወደ ሃገር ቤት መግባታቸው ታውቋል። አቶ ሌንጮ ለታ (የኦነግ መስራችና ፀሀፊ)የነበሩ ዶ/ር ዲማ ናጎ (የኦነግ ሊቀመንበር)የነበሩ ዶ/ር በያን አሶባ (የኦነግ ቃል አቀባይ)የነበሩ ዶ/ር ሀሰን ሁሴን (የኦነግ አመራር አባል)የነበሩ አቶ/ሌንጮ ባቲ (የኦነግ ቃል አቀባይ)የነበሩ። የኦሕዴድ የፖለቲካ የበላይነት የሕዝቡን አመጽ እንደሚያከሽፈውና ጠቅላይ ሚኒስትሩም
Tagged with: , , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

በኢሕአዴግ ተቋም ውስጥ ያለውን ውንብድና ከራሱ ከኢህአዴግ አንደበት ሲጋለጥ

(ከስር ያለው ማመልከቻ አንዲት “ከፍተኛ” አመራር ለዶ/ር አብይ የተፃፈችው ነው። ከእነ ኢህአዴግነቱ ታግሳችሁ ብታነቡት ጥሩ ትዝብት ታገኛላችሁ። እስር ቤት ውስጥ ሆኖ የደረጃ እድገት ያገኘ አለ። ተቋም ውስጥ ያለውን ውንብድና ከራሱ ከኢህአዴግ አንደበት ስሙትማ) ሚያዚያ 19/2010 ለ፡ ክቡር የኢፊዲሪ ጠቅላይ ሚንስትር አቶ አብይ አህመድ ከ፡ ወ/ሮ ሙላቷ ወልዴ አዲስ አበባ ጉዳዩ፡ የተፈጸመብኝ የሰብዓዊ መብት ጥሰትንና ህገ-መንግስቱ ያረጋግጠልኝንበህግ ፊት እኩል የመዳኘት፤ ፍትህ የማግኘት፤ የመልካም ስም ሰብዓዊ መብቴን በዲሞክራሲያዊ መንገድ ማስመለስንይመለከታል፡፡ እኔ ወ/ሮ ሙላቷ ወልዴ ከግንቦት 2002 ዓ.ም ጀምሮ በተለያዩ የፈረደራል ተቋማት በመካከለኛ አመራርነት በተለይም በመልካም አስተዳደርና በለውጥ ስራዎች ላይ ሳገለግል ቆይቻለሁ፡፡ በድርጅት መዋቅር ደግሞ በሰራሁባቸው የተለያዩ የፌደራል ተቋማት የወረዳ የኢህአዴግ ኮሚቴ አመራር በመሆን ሳገለግል የቆየሁ ሲሆን ላለፉት 9አመታትም በአዲስ አበባ ከተማ መስተዳደር የየካ ክፍለ ከተማ የምክር ቤት አባል በመሆን ተመርጬ መንግስትንና ህዝብን በማገልገል ላይ እገኛለሁ፡፡ ከ2002 ጀምሮ እስከ 2005 ዓ.ም በቀድሞው የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን በአሁኑ የአካባቢና ደን ሚኒስቴር ተቋም ውስጥ የለውጥና የመልካም አስተዳደር ስራዎችን በመካከለኛ አመራርነት ደረጃ ስመራና ከፍተኛ አመራሩን በልዩ እረዳትነትና በአማካሪነት ስደግፍ ቆይቻለሁ፡፡ የተቋሙ ራዕይ ማሳኪያ ተግባራት ውስጥ አንዱ በሆነው በAdaptation program ዘርፍ በተቋሙም ተወዳደርሬ በተቀጠርኩበት የስራ ዘርፍ በህጉርና በአለም አቀፍ ደረጃ በአየር ንብረት ለውጥ ድርድሮች ላይ አገሬን በመወከል በመደራደር ለ3 ዓመታት ፈር ቀዳጅ ውጤቶችን ካሲመዘገቡ አመራሮች ውስጥ አንዷ ነኝ፡፡ በዚሀ ተቋም የለውጥና የመልካም አስተዳደር ዳይሬክተር ሆኜ ስመደብ ፤ በወቅቱ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

“የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር” የተባለው ድርጅት በመምጣቱ የሚያተርፈው ማን ነው? (ሳምሶን ኀይሌ)

ሳምሶን ኀይሌ የኢትዮጵያ መንግሥት ከኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኦዴግ) ጋር ድርድር መጀመሩን ግንቦት 6 ቀን 2010 ዓ.ም. ገልጿል፡፡ ኦዴግም ከመንግሥት አንድ ቀን ቀደም ብሎ ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ድርድር እያካሄድ ስለመሆኑ እና የተጀመረውን ድርድር ለመቀጠል አንድ የድርጅቱ የልዑካን ቡድን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጣ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡ ጥያቄው፣ በኦዴግ መምጣት የሚያተርፈው ማን ነው? የሚለው ነው፡፡ መንግሥት ድርድሩን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን በላከው መግለጫ እንዳመለከተው ኦዴግም ሆነ ሌሎች የፖለቲካ ድርጅቶች የአገሪቱን ሕገ መንግሥት ተቀብለው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል ዝግጁ እስከሆኑ ድረስ እንደማንኛውም ተቃዋሚ (ወይም በአዲሱ የመንግሥት አጠራር ተቀናቃኝ) ድርጅት የመንቀሳቀስ መብት አላቸው፡፡ እንደሚታወቀው ከወር በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በአገር ቤት የሚንቀሳቀሱትን ተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎች ቤተ መንግሥት ድረስ ጋብዘው መንግሥት ከተቃዋሚዎች ጋር ለመሥራት ያለውን ቁርጠኝነት ገልጸውላቸው ነበር፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩና መንግሥታቸው ቃላቸውን ይጠብቃሉ አይጠብቁም የሚለው ወደፊት የሚታይ ነው፡፡ ስለሆነም የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የሚባለው በነ አቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው ድርጅት ወደ አገር ቤት ሲገባ እንደማንኛውም የፖለቲካ ድርጅት እንዲንቀሳቀስ ይፈቀድለታል ማለት ነው፡፡ ግን ኦዴግ ምን የተለየ ነገር ያመጣል? ኦሕዴድ አሁን ባለው ቁመና በኦዴግ መምጣት ስጋት ሊገባው ይችላልን? ኦዴግስ ከኦሕዴድ የተለየ ምን አጀንዳ አለው? ከኦሕዴድ በተሻለ መልኩ መብታችን ያስከብርልናል፤ ይወክለናል ብሎ የሚያምነው ምን ያህል ሰው ነው? ኦዴግ በነ ዶ/ር መረራ ጉዲና ከሚመራው ኦፌኮስ ምን የተለየ አጀንዳ አለው? ከኦፌኮ ጋር አብሮ ይሠራል ወይስ ይወዳደራል? ሁለቱ ድርጅቶች ከተጣመሩ መጣመራቸው ምን አዲስ ድርጅታዊ አቅም
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

አብዮታዊ ዴሞክራሲን ማጥፋት ማለት ኢትዮጵያን ማዳን ነው!

ከሔኖክ አበበ የኢህአዴግ ዲሞክራሲ እውነተኛ ዲሞክራሲን ሊያስፍንም ሆነ የሃገሪቱን አንድነት ሊያስጠብቅ አይችልም። ኢህ አዴግም undemocratic እና anti-democracy የሆነበት ዋናው ጉዳይም በሚከተለው አመለካከት የተነሳ ነው። ኢህአዴግ አሁንም ይህንን የማርክሲስም ቅጥያ የሆነ አመለካከት መቀየር የሚቻል በመቃብሬ ላይ ብቻ ነው እያለ ነው። ዶክተር አብይም መስመራችን ትክክልና የማያወላዳ ነው ብሏል። ብአዴን በስሞኑ መግለጫው አብዮታዊ መስመራችን የጠራ ነውና “ከእሱ በፊት እኔን ድፍት ያድርገኝ” እያለን ነው። በተደጋጋሚ እንደምንለው አብዮታዊ ዴሞክራሲ፥ መድብለ ፓርቲን በካልቾ ብሎ ኢህአዴግን አውራ ፓርቲ አድርጎ ማንገስ አላማው ነው። በአንድ አውራ ፓርቲና በሌሎች ኩታራ ፓርቲ ውድድር ዴሞክራሲ ሊሰፍን አይችልም። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ልማታዊ አስተሳሰብ hegemonic መሆን አለበት ብሎ ሌሎች አማራጭ ሃሳቦችን የማይቀበልና ከኔ በላይ ላሳር የሚል አስተሳሰብ ነው። አብዮታዊ ዴሞክራሲ ያልነቃውን ብዙሃን ህዝብ (unconscious mass) የነቁት ጥቂቶች እንደፈለጋቸው ማሽከርከር አለባቸው፡ የግለሰቦች ነጻነት አስፈላጊ አይደለም። ህዝብ መንግስት በፈለገው ሰዓት በሙሉ ሊያፍነው ሆነ ሊኮረኩመው ይገባል በማለት ነጻነትን ደፍጣጭ አስተሳሰብ ነው። ለዚህም ነው ሰሞኑን መንግስት ባዘጋቸው ሰነድ ላይ የፓለቲካ እስረኞችን መፍታት አብዮታዊ መስመርን መሸርሸር ነው የሚል ወለፈንዲ አስተምህሮት እየነዛ የሚገኝ። አብዮታዊ ዲሞክራሲ ማህበረሰብ በመላ እንዲነቃና መብቱን ጠያቂ እንዲሆን አይፈልግም። ማህበረሰብን በነቃ ጥቂት ኢሊት መጮቆን ግን ተቀዳሚ አላማው ነው። አብዮታዊ ዴሞክራሲ የበጎ አድራጎት ድርጅቶች ለሃገር አያስፈልጉም፥ ሚናቸውም ውስን ነው ብሎ የሚያስብ በመሆኑ ኢህአዴግም የበጎ አድራጎት ድርጅቶችና ማህበራት አዋጅ አውጥቶ እንደልባቸው እንዳይንቀሳቀሱ፥ ብዙሃኑን እንዳያነቁና ለመብታቸው እንዲቆሙ እንዳያደርጉ እንቅፋት ደቅኖባቸዋል። በማዕከላዊ
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

የኢህአዴግ የወደፊት ዕጣ ፈንታ (ባይሳ ዋቅ-ወያ)

ባይሳ ዋቅ-ወያ ባገራችን ባለፉት ሶስት ዓመታት ያለማቋረጥ ባገራችን የተካሄደው ሕዝባዊ ዓመጽ ያስከተለው የፖሊቲካ ውስብስብ ይህ ነው አይባልም። ሕዝቡ ያላንዳች አማካይ መሪና የተቀነባበረ አመራር ከዳር እስከዳር ባንድ ላይ ተነስቶ ህገ መንግሥታዊ መብቱን ለማስከበር ፍርሃትን ደፍሮና ደረቱን ለጥይት ገልጦ የተዋጋበት ጊዜ ነበር። ባዶ እጁን ሆኖ እስከ ጥርሱ የታጠቀውን መንግሥት በሰላማዊ ዓመጽ ሲያንገዳግደው፣ በውጥረት የተያዘው ኢህአዴግ ካንዴም ሁለቴ የአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጅ ዓወጀ። ይህም፣ ኢህአዴግ/ወያኔ ዜጎችን እንደተለመደው በጉልበት መግዛትን አለመቻሉንና ሕዝቡም እንደተለመደው ለመገዛት አለመፈለጉን የሚያመለክት፣ ዲ/ን ዳንኤል እንዳሉት፣ የጆሮ ዘመን አልፎ የቀንድ ዘመን መድረሱን አመላካች ሆነ። በኢህአዴግ ውስጥ የህወሃት የበላይነት ቀስ በቀስ እየሟማ መጣ። በደበቢት ምርቶች የተጠፈጠፉት አንጋፋዎቹ የኦህዴድና ብአዴን አባላት በተፈጥሮ ሂደትም ሆነ በሌላ ምክንያት ባገሪቷ የፖሊቲካ ህይወት ውስጥ ንቁ ተሳትፎና ተጽዕኖ አሳዳሪነታቸው እየቀነሰ በመጣ ቁጥር፣ ነጻ የሆኑ፣ ህወሃትን በፍላጎታቸው የተቀላቀሉ ብሎም የህወሃት አባላትን እንደ በላይ አካል የማያዩ የነለማ ቡድን ብቅ ብቅ ማለት ጀመረ። የተፈጥሮ ሂደቱ በተለይም ከመለስ ሞት በኋላ በህወሃት ጎራ ውስጥ ትልቅ ድክመትን እያስከተለ በመምጣቱ፣ በአዲሱ የኦህዴድ-ብአዴን አባላትና በበላይነት እንጂ በእኩልነት መኖር በማይፈልገው የህወሃት አባላት መካከል ያልተጠበቀ “ሁላችንም እኩል ነን” የሚል አዲስ የግንኙነት መስመር ሳይታሰብ ተሰመረ። የህወሃት አባላት፣ የነበራቸውን የበላይነት ተጠቅመው በየክልሉ አስተዳደር ጣልቃ እየገቡ በባለሥልጣናቱና በህዝቡ ላይ ያሳደሩትን ጫና ተከትሎ የተከፋውን ህዝብ ድምጽ ለማስማት፣ በነለማ የተመራው አዲስ ትውልድ “በህገ መንግሥቱ መሰረት ክልላችንን ያላንዳች የውጭ ተጽዕኖ እናስተዳድር” ብለው በመነሳታቸው፣ ኢህአዴግ ውስጥ
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

እየታየ ያለው ለውጥ፤ የቅርጽ ወይስ የይዘት? – ብርሃኑ አበጋዝ

ዶ/ር ብርሃኑ አበጋዝ – አዲስ አበባ ጭብጥ *** የጽሑፌ ጭብጥ፣ አሁን በአገራችን እየታየ ያለው ለውጥ የቅርጽ እንጂ የይዘት አይደለም የሚል ነው፡፡ መግቢያ *** አንድ፣ ተርታው (ordinary) ዜጋ ሳይቀር እተገነዘበው የመጣ ሐቅ አለ፡፡ ይህም ሐቅ ገዥውን ግንባር የተመለከተ ነው፡፡ ኢሕአዴግ ደንብሿል፤ አርጧል፤ አዲስ ሐሳብ ማመንጨት አይችልም፡፡ ይኽ እውነት ነው፡፡ ገዥው ግንባር ዘመኑን የዋጀ ሐሳብ የሚያፈልቅ አዲስ ኀይል ማፍራት የማይችል ድርጅት ሆኗል፡፡ አሁንም የድርጅቱ ከፍተኛም ይኹን ዝቅተኛ አመራሮች አቶ መለስ ባዘጋጇቸው መጻሕፍት ነው ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙት፡፡ አዲስ ራዕይ የተባለው የድርጅቱ የንድፈ-ሐሳብ መጽሔት ሳይቀር አቶ መለስ በሕይወት በነበሩበት ጊዜ ያዘጋጇቸውን ጽሑፎች እንደገና እየቀባባ ማወጣት ጀምሯል፡፡ ጥልቅ ተሐድሶ የሚለው “አዲሱ” የኢሕአዴግ መርሐ ግብርም በአቶ መለስ አስተምህሮዎች ላይ የተንጠለጠለ እና የእሳቸውን ጽሑፎች መሠረት ያደረገ ነው፡፡ የሚገርመው የገዥው ግንባር መሪዎች ለስልጠና ሳይቀር አቶ መለስ የተናገሯቸውን ንግግሮች (ቪዲዮዎች) በመጠቀም ላይ ናቸው፡፡ አሁንም የሐሳቡ አምንጭም አሰልጣኙም አቶ መለስ ናቸው፡፡ አንዳንዴም በብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያው ሳይቀር የአቶ መለስ ንግግሮች ይቀርባሉ፡፡ ጥልቅ ተሐድሶ በሚባለው መርሐ ግብር ከቀረቡት ነጥቦች ውስጥ “መስመር መሳት” የሚል ይገኝበታል፡፡ መስመር መሳት የተባለውም በአቶ መለስ የተዘጋጁትን ፖሊሲዎችና ፕሮግራሞች መተው ማለት ነው፡፡ አዲስ ሐሳብ፣ ከዘመኑ ጋር ሊሄድ የሚችል አቀራረብ ከድርጅቱ መስመር እንደመውጣት ይቆጠራል፤ ያስገመግማል፡፡ “ዴሞክራሲያዊ ልማታዊነት እና/ወይም አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ከሚባለው መስመር ውጭ የሚታሰብ ነገር የለም፡፡ የግንባሩ ከፍተኛ አመራሮችም ሆኑ አፈ ጮሌ (እና አድርባይ) ካድሬዎች የሚናገሩት ሁሉ የዛገና አዲስ ነገር
Tagged with: , , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ጉምቱ የሚባሉት የኢህአዴግ ነባር ታጋዮች አሁን ለምን ዝምታን መረጡ? ጎንበስ ያለ ያደፈጠ ኃይል ይኖር ይሆን?

ዶ/ር አብይ ከቃል ብዙ ነገር እያስተማሩን ነው፤የኔ ስጋት ግን ይሄ የዜግነት፣ሃገራዊነት አጀንዳ የማን አጀንዳ ነው? የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ የዶ/ር አብይና የጥቂት የራሳቸው ቡድኖች አጀንዳ ነው? ወይስ የኢህአዴግም ነው? ይሄ ያስጨንቀኛል፡፡ ኢትዮጵያዊነትና የሃገር ታሪክ፣የኢህአዴግ አጀንዳ ነው ወይ? ከጥቂት ወራት በፊት እኮ “ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር” ማለት የነፍጠኛ ምልክት ተደርጎ ነበር የሚወሰደው፡፡ “ፈጣሪ ህዝቧንና ሃገሪቱን ይባርክ” ማለት እኮ ለድርጅቱ አባላት አስቂኝ ነበር፡፡ በእርግጥ አሁን ዶ/ር አብይ ይሄን ሲሉ፣ኢህአዴጎች እንደ ሌላው ኢትዮጵያዊ ተቀብለውታል ወይ? ለምንድነው በዚህ ላይ ሃሳብ አስተያየት ከመስጠት ተቆጥበው በዝምታ የተዋጡት? ጉምቱ የሚባሉት የኢህአዴግ ነባር ታጋዮች፣አሁን ለምን ዝምታን መረጡ? የመንግስት ሚዲያውስ ለእነዚህ የጠቅላይ ሚኒስቴሩ ንግግሮች የዜና ሽፋን በመለስ ጠለቅ ያለ ትንታኔ ሲያቀርቡ ለምን አናይም? ምንድነው ዝም ብሎ የመታዘቡ ምስጢር? የሚለው ነገር በጣም ያሳስበኛል፡፡ ይሄን ሂደት ለማደናቀፍ የተዘጋጀ ድብቅ ኃይል ይኖር ይሆን? የሚል ጥያቄ አለኝ፡፡ይሄን ኢህአዴግም ዶ/ር አብይም ሊመልሱት ይገባል፡፡ የዶ/ር አብይ ቡድን በኢህአዴግ ውስጥ ያለውን ያረጀ አስተሳሰብ አሸንፎታል ብሎ ማሰብ የዋህነት ነው፡፡ ሊያሸንፍ አይችልም፡፡ የፖለቲካ ታሪካችንም ይሄን አያሳይም፡፡ ምናልባት የህዝቡ ስሜት ስለጎለበተና ወጀቡ ስለበዛ ጎንበስ ያለ ያደፈጠ ኃይል ይኖር ይሆን? የሚለው በጣም ያሰጋኛል፡፡ ይሄ ያደፈጠ ኃይል አቶ ለማንና ዶ/ር አብይን አንገዋሎ ነቅሎ እስከማስወገድ የሚደርስ ጉልበት እንዳይኖረው እሰጋለሁ፡፡ የዚህ ስጋት ደግሞ ምልክቱ እየታየ ነው፡፡ ዶ/ር አብይ የሃይማኖት ድርጅት አይደለም የሚመራው፣ሃገር ነው፡፡ ከተራራ ላይ በሚዘንብ ስብከትና ምስባክ ብቻ እስከመጨረሻው ይዞን ሊዘልቅ አይችልም፤በተግባር ማሳየት አለበት፡፡
Tagged with: , ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ገዢው ፓርቲ፤ “ከአገርህ? ከሥልጣንህ?” ተብሎ ይጠየቅልን ( ኤልያስ )

• ለወጣቶች ከተመደበው 10 ቢ.ብር ውስጥ 4 ቢ.ብር ሥራ ላይ አልዋለም •ኢህአዴግ በኛ ጉዳይ፣ ከኛ ተደብቆ ይወስናል!! • ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የምናተርፈውን በግልጽ እንወቀው Addis Admass በርግጥ ዛሬ ያመጣው አመል አይደለም፡፡ ኢህአዴግ ነፍሴ ሁሌም እንዲሁ ነው! ላለፉት 27 ዓመታት የኖረበት ዘዬው ነው፡፡ በቃ ድብቅ ፓርቲ ነው – ምስጢረኛ! ድብቅነት ባህሉ ነው፡፡ ስብሰባውና ግምገማው ሁሉ በዝግ በር ነው፡፡ በፓርቲው ጉዳይ ብቻ ቢሆን ግዴለም ነበር፡፡ ግን የኛን ጉዳይ ጭምር (የህዝቡን ማለቴ ነው!) የሚወስነው ለብቻው ነው – በምስጢር!! በህዝብ ጉዳይ፣ ከህዝብ ተደብቆ ለብቻው ይወስናል – ኢህአዴግ ነፍሴ! ለምሳሌ አዲሱን የኢህአዴግ ሊ/ቀመንበር የመረጠው ከኛ ተደብቆ ነው – በምስጢር! (የኛን ጠ/ሚኒስትር፣ከኛ ተደብቆ ይመርጥልናል!) ከመረጠ በኋላም ምስጢሩ ይቀጥላል፡፡ ቀድሞ የሚነገራቸው ጥቂት ሚዲያዎች አሉ። (“ልማታዊ ሚዲያዎች”?!) ኢህአዴግ ነፍሴ፤እነሱን ብቻ በምስጢር ጠርቶ መረጃውን ያቀብላቸዋል፡፡ (“የባለቤቱ ልጆች” በሉዋቸው!) አንዳንዴ ኢህአዴግ፤ የድሮ ወላጆችን ይመስለኛል – “ባህላዊ ወላጆች”! (የወላጅ አንጀት ግን ኖሮት አያውቅም!) የድሮ ወላጆች፤ ለልጆቻቸው ባል ወይም ሚስት የሚያጩት፣ ልጆቻቸውን አማክረው ወይም አሳትፈው አይደለም፡፡ በራሳቸው ፍላጎትና ምርጫ ብቻ ነው። ኢህአዴግም በህዝብና በአገር ጉዳይ፣በራሱ ፍላጎትና ምርጫ ብቻ ይወስናል፡፡ (ደስ ያለውን!) በርግጥ በአሁን ዘመን ለልጆቹ የትዳር ጓደኛ ለመምረጥ የሚደፍር ወላጅ የለም፡፡ የሚደፍር እንኳን ቢኖር የሚቀበለው አይኖርም። በዚያ ላይ መሳቂያ ነው የሚሆነው። ኢህአዴግ ነፍሴ ግን አሁንም ኮስተር ብሎ በህዝብ ጉዳይ፣በምስጢር እየመከረ መወሰኑን ቀጥሎበታል። (ያለኛ ፈቃድ!) አንዳንዴ ሳስበው… ሥልጣን የህዝብ መሆኑን ሁሉ የረሳው ይመስለኛል፡፡
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ሥርዓቱ የገባበት አጣብቂኝ (ጌታቸው አስፋው)

ሥርዓቱ የገባበት አጣብቂኝ (ጌታቸው አስፋው) ሀ.) የፖለቲካ አጣብቂኝ *** ኢሕአዴግ ብዙ እውነት ያልሆኑ ነገሮችን ለአዲሱ ትውልድ ስለነገረ በጊዜው የነበርን ሰዎች እውነቱን ተናግረን ወጣቱ በሐሰተኛ ወሬ ውዥንብር ውስጥ እንዳይገባና እንዲያገናዝብ ልንረዳው ይገባል፡፡ አውራ የሆነው የሐሰት ወሬ ደግሞ ደግሞ ከሃያ ሰባት ዓመት በፊት ኢሕአዴግ ኢትዮጵያን ባይቆጣጠር ኖሮ አገሪቱ በብሔረሰብ ብጥብጥ ልትፈራርስ ተቃርባ ነበር የሚለው ነው፡፡ የኢሕአዴግ አባላት ዓይናቸውን በጨው አጥበው ሚዲያ ላይ ቀርበው እኛ ባንገባ ኢትዮጵያ ልትፈራርስ ተቃርባ ነበር ብለው እንደሚናገሩ በቅርቡ በፓርቲያቸው አስገዳጅነት ከፌዴሬሽን ምክር ቤት ሰብሳቢነትና ከሚኒስትርነት ቁልቁል ወርደው አምባሳደር ሆነው ወደሚጠሉት ኒዮ-ሊብራሎች አገር ኑሮን ለመጋራት ሊሄዱ እንደተነሱ ለ‹ኢ ኤን ኤን› ጋዜጠኛ ቃለ ምልልስ ከተናገሩት ከአቶ ካሳ ተክለብርሃን አንደበት ነው የሰማሁት፡፡ ከ1950ዎቹ በፊት ስለነበረው በዓይን አይቼ ስለማላውቅ ከዚያ በኋላ በተወለድኩበት ከፋ ጠቅላይ ግዛት የማውቀውን እጽፋለሁ፡፡ የዚያን ዘመን ኢትዮጵያ በባላባታዊ የኢኮኖሚ ሥርዓት የምትተዳደር መሆኑን እና ባላባቶቹ ተወላጆቹ ነበሩ ወይንስ መጤዎች ለሚለው ጥያቄ መልስ መስጠት የኢሕአዴግን በሬ-ወለደ የፈጠራ ወሬ ያከሽፋል ብዬ አምናለሁ፡፡ ከፋ ጠቅላይ ግዛት የዛሬን ሁለት ክልሎች ከደቡብ ከዳውሮ እስከ ከፋና ማጂን፣ በሰሜን የምን፣ ከአሮሚያ የጂማ አውራጃን፣ ያካለለ ነበር በ1950ዎቹ የጠቅላይ ግዛቱ ዋናው ባለሥልጣን የንጉሠ ነገሥቱ እንደራሴ የነበሩት የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ደጃዝማች ክፍሌ ዳዲ ነበሩ፡፡ በ1960ዎቹ ደግሞ አማራው ደጃዝማች ፀሐዩ ዕንቁሥላሴ ተተኩ፡፡ የጠቅላይ ግዛቱ ዋና ከተማ የነበረችውን የጂማ አውራጃን ከነ ወረዳዎቿ በበላይነት ያስተዳደሩት የአባ ጂፋር ልጅ ደጃዝማች አባ ጀበል አባ ጂፋር
Tagged with: ,
Posted in Amharic News, Ethiopian News

ባለፉት አመታቶች የወጣቱ ደም ደመከልብ የሆነው አዲስ የእጅ አዙር አምባገነኖችን ለመፍጠር አይደለም።

ምንሊክ ሳልሳዊ ፦ የትግሉ አነሳስና የትግሉ ግብ ወያኔን ማስወገድ ነው ። የፈዘዘ ቀረ እንደደነዘዘ። ባለፉት አመታቶች የወጣቱ ደም ደመከልብ የሆነው አዲስ የእጅ አዙር አምባገነኖችን ለመፍጠር አይደለም። ወያኔ ከየአቅጣጫው የምያየውን የተስፋ ድጋፍ ለፖለቲካ ፍጆታ እንደሚጠቀምበት ልናውቅ ይገባል። የአብይ ጉዳይ በፍጹም ሊያነጋግረን አይገባም። ዋናው ጉዳያችን የሆነውን ወያኔን ከስሩ ነቅሎ የመጣል ትግላችንን አጠናክረን መቀጠል ይገባናል። ተቃዋሚ ነን የሚሉ ፖለቲከኞች ለሁለት ተከፍለዋል። የስልጣን እና የጥቅም አምሮት ያወረው ሃገር ቤት ያለው ተቃዋሚ ነን ባይ (በጣት ከሚቆጠሩ ግለሰቦች) በስተቀር ሁሉም ሆዳምና አጨብጫቢ ነው ፤ ወደ ዲያስፖራው ስንመጣም እንዲሁ (በጣት ከሚቆጠሩት) ውጪ በተገኘበት የሚነፍስ እየተበራከተ መጥቷል። የትግሉ አነሳስና የትግሉ ግብ ወያኔና ማስወገድ ነው ብለን እስከተነሳን ድረስ በግንባር ቀደምትነት ትግላችንን ማጣናከር ይጠበቅብናል። የአብይም ሆነ የኢሕአዴግ ጉዳይ ለጥቃቅን የፖለቲካ ግብአቶችና ለመረጃ ማስፋፊያ ካልሆነ በስተቀር ለእኛ ምንም የሚጠቅመን ጉዳይ የለም። አብይ ጥቅሙ ለኢሕአዴግ ብቻ ነው። ለስር ነቀል የፖለቲካ ለውጥ ለስር ነቀል የኢኮኖሚ ለውጥ የሰለጠነ ማሕበረሰብ ፈጠራ ግቦችን ለማሳካት መጀመሪያ ስርዓቱን ነቅለን እናስወግድ ፤ አጉል ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ነው ፤ ሳንበላው ዳቦውም ይሻግታል ፤ እኛም በረሃብ እናልቃለን። ፈጥነን እውነትን ተቀብለን ትግላችንን እናጠናክር ፤ ስንዘናጋ ሃገርና ህዝብ አደጋ እየተጋረጠባቸው መሆኑን አንዘንጋ። #MinilikSalsawi
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News

ወያኔ የኢትዮጵያዊነት ጭምብል አጥልቃ ስልጣን ላይ ለመቆየት አስፈላጊውን ዝግጅት አጠናቃ ጨርሳለች።

የቄሮ ” ሞተር ” ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ ከሶስት መቶ በላይ የኦሮሚያ አክቲቪስቶች ስዩምና ታዬን ጨምሮ ዘብጥያ ከተወረወሩ ከረመ። ቄሮም ዕድሜ ለድል አጥቢያ አርበኞቹ የዕንቅልፍ ክኒን ውጦ አሸልቧል። በዚያኛው ጫፍ ደግሞ በረከት ስምዖን የአማራውን አከርካሪ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመስበር በአዲስ ጉልበት እየተንቀሳቀሰ ይገኛል። በአንዳንድ ቦታዎች የዘር ግጭቶች እያቆጠቆጡ ለመሆናቸው ምልክቶች ይታያሉ ። የአረማያ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ዳቦ ስለጠየቁ ብቻ በቆመጥ ተደብድበዋል ። አያንቱ ደሟ ደመ ከልብ ሆኖ ቀርቷል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የማረጋጋት ተልዕኳቸውን ተፅፎ በሚቀርብላቸው ጣፋጭ መጣጥፍና በእራት ግብዣ አስደግፈው እየተወጡት ነው። የትግራይ ሰማዕታት ሐውልት ላይ የአበባ ጉንጉን ያስቀመጡት ጠቅላይ ሚኒስትር በተስፋዬ ገብረአብ ተረት ተመስርቶ የተገነባውን አኖሌ ሐውልት ለማፍረስ እስካሁን ድፍረት አላገኙም ወይም ፈቃደኛ አይደሉም ።በቀለና መረራን የመሰሉ ታጋዮች ልደቱና በየነን ከመሰሉ አድርባዮች ጋር በአንድ አዳራሽ ውስጥ ተቀምጠው የፖለቲካ ሽርሙጥናን ሲያስተናግዱ ወይም ሲጫንባቸው ማየት ያማል ። ወያኔ አዲስ ንጉሥ አንግሶ አገር ተረጋግቷል በተባለበት ወቅት እንኳን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁን ለማንሳት ፈቃደኛ አልሆነም ። የአንዳርጋቸው ፅጌ ልጆች ያለአባት ሲያድጉ ያደላቸው ደግሞ ቤተመንግስት ውስጥ ቁጭ ብለው ኬክ ይቆርሳሉ። በጠቅላይ ሚኒስትሩ ፍቅር የተነደፉት የዳያስፖራ ደጋፊዎች የቀራቸው ነገር ቢኖር በትከሻቸው ተሸክመውት መዞር ብቻ ነው። ሕፃን ልጅ በከረሜላ እንደሚታለል ሁሉ እነዚህም በጣፋጭ ቃላት ይነሆልላሉ ብሎ ማን ጠረጠረ?! አንዳንዶቹ ድጋፋቸው መረን ከመልቀቁ የተነሳ ጭራሽ ወጥ እየረገጡ ያለበት ሁኔታ ነው ያለው። በአጠቃላይ የዘጠና ሰባቱን እንቅስቃሴ በእነልደቱ አማካይነት ያኮላሸችው ወያኔ አሁንም አዲስ
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News

የይስሙላ ለውጥ እንዳይሆን! (አሸናፊ ሞላ)

የይስሙላ ለውጥ እንዳይሆን ! ( አሸናፊ ሞላ) ሕዝባዊ አመጹንና የፖለቲካ ቀውሱን ለማስታገስ ሲባል በተለይ በወለፈንድ ርዕዮተ ዐለም ላይ የተቸከለው የሕወሃት ነባር አመራር በመልካም ፍቃዱ ለሥልጣን እንዳበቃቸው መረሳት የለበትም፡፡ ዶ/ር አብይ አህመድ የኢሕአዴግ ሊቀመንበርና የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ከሆኑ በኋላ በርካታ ቁጥር ያለው የአገራችን ሕዝብ በተስፋ ስሜት ላይ ቢሆንም፣ ኢትዮጵያ ያለችበት ሁኔታ ከምንጊዜውም በላይ በጣም አሳሳቢ ነው፡፡ በተለይ ካለፉት ሁለት ዓመታት ጀምሮ የሚታየው ነገር ከባድ ከመሆኑም በላይ መሠረታዊ ለውጥን የሚጋብዝ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ወጣቶች መሠረታዊ ጥያቄዎችን አንግበው ሲታገሉና ሲሞቱ ቆይተዋል፡፡ ተቃውሞው በተወሰነ ደረጃ ጋብ ያለ ቢመስልም ቆሟል ማለት ግን አይቻልም፡፡ ከሁሉ አስቀድሞ ይኽን የለውጥ ጥያቄ የሚያነሳው የትኛው የኅብረተሰብ ክፍል ነው? የሚለውን ነጥብ መለየቱ ተገቢ ነው፡፡ የለውጡ እንቅስቃሴ ሞተር ወጣቱ ነው፡፡ ይኽ ወጣት የኅብረተሰብ ክፍል መቶ ሚሊዮን እንደሚሆን ከሚገመተው የአገራችን ሕዝብ ውስጥ 70 መቶ የሚሆን ድርሻ አለው፡፡ ይኽ በገጠርም በከተማም የሚኖረው ወጣት ነገሮች ቢመቻቹለት በአጭር ጊዜ ወደ መካከለኛ መደብ ሊደርስ የሚችል ነው፡፡ አፍሪካ ውስጥ እንደሚታወቀው የመካከለኛ መደቡ ቁጥር አነስተኛ ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያ ደግሞ በጣም አነስተኛ ነው፡፡ ነገሮች ቢመቻቹለት፣ ትክክለኛ ኢኮኖሚ ፖሊሲ ቢቀየስለት፣ ትክክለኛ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓት ቢዘረጋለት በአጭር ጊዜ ውስጥ መካከለኛ ገቢ ሊኖረው የሚችል የኅብረተሰብ ክፍል ነው፤ ወጣቱ፡፡ የሚጠይቀውም ትክክለኛ ጥያቄ ነው፡፡ በገጠር ያለው አብዛኛው መሬት ይፈልጋል፡፡ በከተማ የሚኖረውም ካፒታል እንዲፈጥርና ራሱን እንዲችል ሁኔታዎች ሊመቻቹለት ይገባል፡፡ ወጣቱ የኅብረተሰብ ክፍል ጥራት ያለው ትምህርትም ባይሆን ተምሯል፤ በተለያየ
Tagged with: , ,
Posted in Ethiopian News

ኢሕአዴግ ተጠናከረ ? (ሳምሶን ኃይሌ)

ኢሕአዴግ ተጠናከረ? *** ሳምሶን ኃይሌ *** መግቢያ *** ኢሕአዴግ በመወጪው ወር ሥልጣን የያዘበትን 27ኛ ዓመት ያከብራል፡፡ ግንባሩ በኢትዮጵያችን ታሪክ ከቀዳማዊ ኃይለሥላሴ መንግሥት ቀጥሎ ለረዥም ዘመናት በሥልጣን ላይ ቆይቷል፡፡ አሁንም ላልተወሰኑ ዓመታት በሥልጣን ላይ የሚቆይበትን ዕድል አግኝቷል፡፡ ከ27 ዓመት በፊት የነበረው ዓለም ዐቀፋዊ የፖለቲካ ሁኔታ፣ የሶቪየት ኅብረት ፊታውራሪነት ይመራ የነበረው የሶሻሊስት ክምፕ የተንኮታኮተበትና በአሜሪካና አጋሮቿ የሚመራው የሊብራል ዴሞክራሲ ካምፕ በአሸናፊነት የወጣበት፣ እንደ ፍራንሲስ ፉኩያማ ያሉ ምሁራን በከፍተኛ የእርግጠኝነት ስሜት “የዓለማችን የመጨረሻውና ብቸኛው አማራጭ ሊብራል ዴሞክራሲ መሆኑ ተረጋግጧል” ብለው የተከራከሩበት ጊዜ ነበር፡፡ ብዙሃኑ የዓለማችን አገራት የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን መቀበላቸውን እየተሸቀዳደሙ የሚገልፁበትና የምዕራዊያንን ሞገስ (እና እርዳታና ድጋፍ) ለማግኘት የሚራወጡበት ጊዜም ነበር፡፡ እንደፕ/ት ቢል ክሊንተን ያሉ ‹ሊብራል ሉላዊያን› (liberal globalist) መሪዎችና የእነሱን አስተሳሰብ የሚያራምዱ ዓለም ዐቀፍ መንግሥታዊና መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች “ዴሞክራሲን በዓለም ላይ ለማስፋፋት” ከፍተኛ እንቅስቃሴ አድርገዋል፡፡ አገራቱ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓትን የሚፈቅድ ሕገ መንግሥት እንዲያፀድቁ፣ አገር በቀልና ዓለም ዐቀፍ መንግሥታዊ ያልሆኑ ድርጅቶችና ልዩ ልዩ ሲቪል ማኅበራት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ የፖለቲካ ሁኔታ እንዲፈጠር፣ ጋዜጠኞችና የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች በነጻነት የሚንቀሳቀሱበት ምቹ ሁኔታ እንዲመቻች ወዘተ. ግፊት ተደርጓል፡፡ ፕሮፌሰር ሳሙኤል ሃንቲንግተን “ሦስተኛው ሞገድ” ሲሉ የገለጹት የዴሞክራሲ ሽግግር የፓርቱጋሉ አምባገነናዊ አገዛዝ ከወደቀበት ሚያዚያ 1966 ዓ.ም. እንደጀመረና ሒደቱ ወደግሪክ፣ ስፔንና የላቲን አሜሪካ አገሮች እንደተሸጋገረ ጽፈዋል፡፡ ሃንቲንግተን The Third Wave (1991) በሚለው መጽሐፋቸው እንዳብራሩት፣ ከሦስተኛው የዴሞክራሲ ሞገድ በፊት አብዛኞቹ የዓለም አገሮች በወታደራዊ፣
Tagged with: , , ,
Posted in Ethiopian News

የዶክተር አቢይ ይቅርታና ኢሕአዴግ ልጆቻቸውን የገደለባቸው ወላጆች መልስ

አዲሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አሕመድ በፓርላማ ሲሰየሙ ባደረጉት ንግግር በኢትዮጵያ ሕወታቸው ለተቀጠፈ ሰዎች መፀፀታቸውን ገልፀው ይቅርታ ጠይቀዋል። በቅርቡ ልጆቻቸው ከተገደሉባቸው መካከልይቅርታ ብቻውን ለደማ ልብ መጠገኛ ሊሆን አይችልም ይቅርታው ተቀባይነት የሚኖረው ድርጊቱን የፈፀሙ ሰዎች ለፍርድ ሲቀርቡ ነው ብለዋል። “የገደሉት ልጄ አስከሬን ላይ ቁጭ በይ ብለው ደበደቡኝ” ሲሉ ከዚህ ቀደም በደንቢዶ ዶሎ ከተማ ስለተገደለ የ16 ዓመት ኃይሉ ኤፍሬም አሟሟት የተናገሩት እናንት ወይዘሮ ታደሉ ተማምን ስለ ዶ/ር አብይ የይቅርታ መልዕክት ተጠይቀው “እኔ ሁሉም ነገር የተደበላለቀብኝ ሰው ነኝ የምናገረው የለኝም።” ብለዋል። በመርሳ ከተማ በሐብሩ ወረዳ የተገደለው የ23 ዓመቱ ወጣት አብዱ ሞላ ወላጅ አባት አቶ ሞላ ንጋቱ፣ በነቀምት ከተማ የተገደለ የ13 ኦኣመት ወጣት አብሳ እንዳለ አባት አቶ እንዳለ ፉፋ እንዲሁም በወልዲያ ከተማ የተገደለው የ35 ዓመቱ ገብረመስቀል ጌታቸው አባት አቶ ጌታቸው ኃይሌ ስለ ዶ/ር አብይ ይቅርታ ተጠይቀዋል። የሰጡትን ምላሽ ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያድምጡ። https://av.voanews.com/clips/VAM/2018/04/04/6a18a3f1-d36d-4559-89ea-01c20b7dbb70_32k.mp3?download=1
Tagged with: , , ,
Posted in Ethiopian News

ታጥቦ ጭቃው ከኢህአዴግ ምክር ቤት ድርጅታዊ መግለጫ

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ ድርጅታዊ መግለጫ የኢህአዴግ ምክር ቤት ከመጋቢት 11 ቀን እስከ መጋቢት18 ቀን 2010 ዓ.ም ድረስ መደበኛ ስብሰባውን አካሂዷል፡፡ በዚህ ስብሰባ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባቀረባቸው ሁለት ሪፖርቶችና ከድርጅታችን ሊቀ መንበር የስራ መልቀቂያ ጋር በተያያዘ የመተካካት አጀንዳ ላይ ሰፊ ውይይት አካሂዶ ስብሰባውን በመግባባትና በአንድነት መንፈስ አጠናቋል፡፡ ምክር ቤታችን በቅድሚያ የመከረበት አጀንዳ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው በታህሳስ ወር ያካሄደውን ግምገማ መነሻ በማድረግና በየብሄራዊ ድርጅቱ የተካሄደውን ራስን ፈትሾ የማስተካከል እንቅስቃሴ ባካተተው ሪፖርት ላይ ነበር፡፡ በዚህ ሪፖርት አገራችን ባለፉት 27 አመታት በተጓዘችበት ሂደት የተመዘገቡ ለውጦች እንዲሁም በአሁኑ ጊዜ ያጋጠሙን ፈተናዎችና በእጃችን የገቡ መልካም እድሎች በዝርዝር ቀርበው በሰፊው ተመክሮባቸዋል፡፡ ድርጅታችን ኢህአዴግ በየምርጫው የህዝብ ድምፅ አግኝቶ አገር የመምራት ኃላፊነቱን ከተረከበበት ጊዜ ጀምሮ በተካሄዱ ጥረቶች ለማንም ግልፅ እንደሚሆነው በሁሉም የህይወት መስኮች አገራዊ ተስፋችንን ያለመለሙ ለውጦች ተመዝግበዋል፡፡ ይህ ለውጥ ከምንም ነገር በፊት የጀመረው አገራዊ የዴሞክራሲ ትንሳኤን ያበሰረ ዴሞክራሲያዊ ህገ መንግስት ባለቤቶች በመሆናችንና አቅም በፈቀደ መጠን ይህንኑ ተግባራዊ በማድረግ የዜጎችና የህዝቦች መብትና ተሳትፎ የተከበረበት ሁኔታ በመፈጠሩ ነው፡፡ አገራችን የሁሉንም ህዝቦች ተሳትፎ ባረጋገጠ አኳኋን ባፀደቀችው ህገ መንግስት የዜጎችና የህዝብ ሰብአዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች የተሟላ እውቅና ተሰጥቷቸዋል፡፡ በብዝሃነት በተዋቀረችው አገራችን ውስጥ የዘመናት የህዝቦች ጥያቄ ሆነው የቆዩት የእኩልነት መብቶች ተከብረዋል፡፡ የብሄሮች፣ የኃይማኖቶች፣ የፆታና መሰል የእኩልነት መብቶች ህገ መንግስታዊ እውቅናና ዋስትና ተሰጥቷቸዋል፡፡ አገራችን የብዙ ፍላጎቶችና ጥቅሞች መናሃሪያ መሆኗን በመቀበል የመድብለ ፓርቲ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት
Tagged with: ,
Posted in Ethiopian News