ለኦሮምኛ የሚያዋጣው የግእዝ ፊደል ነው- አበበ ቶሎሳ ፈይሳ

የበደል ነጋዴዎች አባዝተው በደሉን ሸጠውልን እንጂ… እንዲህም ነበርን!

በጣም የሚቆጨኝ Dha የሚለውን የኦሮምኛ ቃል የምትወክል ፊደል በግዕዝ ፊደላት ተካታ ለረጅም ግዜ ቆይታ ወደ ታይፕ ቴክኖሎጂ ሳትገባ ቁቤ መጥቶ መጥፋቷ!

እውነት እውነት እላችኋለሁ ኦሮምኛን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቋንቋዎች አንዱ ለማድረግ የግዕዝ ፊደላትን ቢጠቀም በጣም የተሻለ ይመስለኛል። አሁንም ቢሆን ቀና አሳቢ ኦሮሞ ፀሃፊዎች ፅሁፎቻችሁን በግዕዝ ፊደላት ጭምር ብትፅፉልን… ወደፊትም ከላቲን ፊደላት ጎን ለጎን የግዕዝ ፊደላትም ለኦሮምኛ ቋንቋ ግልጋሎት ቢሰጡ እና ቀስ በቀስ ዳግም ወደ ሃገር በቀል ፊደላችን ብንመለስ ምኞቴ ነው።

ችግሩ ፖለቲካው እና ሳይንሱ ተምታተው እና ተደበላልቀው ነው እንጂ ትክክለኛ ሳይንሳዊ ጥናት ቢደረግ ለኦሮምኛም ሆነ ለሌሎቹ ሃገር በቀል ቋንቋዎች የሚያዋጣቸው የግዕዝ ፊደላትን መጠቀም ይመስለኛል።

ብንተባበር…አፍሪካችን ያፈራቻቸውን ፊደላት ለመላው አፍሪካ ሁላ ኩራት ማድረግ እንችል ነበር!


► መረጃ ፎረም - JOIN US