ሕገ ወጥ ሰፈራ በባቢሌ የዝሆኖች መጠለያ ላይ ስጋት መፍጠሩ ተገለጸ

በኢትዮጵያ ትልቁ የባቢሌ ዝሆኖች መጠለያ፣ ለኢንቨስተሮች ተቆርሶ የተሰጠው መሬት ቢመለስም አሁንም የቀጠለው ሕገወጥ ሰፈራ ህልውናውን አደጋ ላይ መጣሉን፣ የመጠለያው ኃላፊ አቶ ባንኪ ቡዳሞ ለአሜሪካ ድምፅ ገልጸዋል።