የኦነግ ሸኔ ኃይሎች ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት ያገቷቸውን ቀዳሽ ካህናትና 8 አስቀዳሽ ምእመናንን

የግድያ ዜና

“…የካቲት 17/2016 ዓም እሁድ ንጋት ላይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ኢሉ ወረዳ በአስጎሪ ርጳ ቅዱስ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ካህናቱ ጸሎተ ኪዳን አድርሰው ቅዳሴ ሊገቡ ሲሉ የታጠቁ የኦነግ ሸኔ ኃይሎች ወደ ቤተ መቅደስ በመግባት 5 ቀዳሽ ካህናትና 8 አስቀዳሽ ምእመናንን አግተው ወሰዱ። ቆይተው ስምንቱ ምእመናንና የደብሩ አስተዳዳሪ አጋቾቹ የጠየቁት ገንዘብ ተከፍሏቸው ይለቋቸዋል። ለተቀሩት አገልጋይ ካህናትን የማስለቀቂያ ገንዘብ ቢከፈልም ሳይለቋቸው ቅዳሜ መጋቢት 14/2016 ዓም በአሰቃቂ ሁኔታ ገድለዋቸዋል።

• የተገደሉት አገልጋዮች ስም…

1.ቀሲስ ቸርነት ብዙወርቅ ቄሰ ገበዝ
2.ቀሲስ ሳሙኤል ወደጆ ቀዳሽ ካህን
3.መሪጌታ ያሬድ የደብሩ መሪጌታ እንዲሁም
4.ዲ/ን ቤዛ ባዬ የደብሩ ጠቅላላ አገልግሎት ናቸው።

“…በተለይም የደብሩን መሪጌታ መጀመሪያ እጃቸውን ቆርጠው ለውሻ በመስጠት ከዚያ በኋም እያንዳንዱን አካላቸውን በገጀራ በመቆራረጥ እንደገደሏቸው የዐይን እማኞች መግለጻቸውን፣ ሌሎቹንም አገልጋዮች በተመሳሳይ ሁኔታ እጅግ አሰቃቂ በሆነ መንገድ እንደተገደሉ፣ ከዚህ በተጨማሪም በቾ ወረዳ ሶየማ እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያን ቀሲስ መልአኩ የተባሉ አንድ ካህን መጋቢት 17/2016 ዓም ሌሊት ታግተው ተወስደዋል። ቶሌ ወረዳ ላይ እንዲሁ አንድ ዲያቆን በመውሰድ ለመልቀቅ 1 ሚልዮን ብር እንደጠየቁ ለማወቅ ተችሏል በማለት ስምዐ ተዋሕዶ ዘግቧል።

“…ብፁዕ አቡነ ጴጥሮስ የአማሪካ ዜግነቴን እንደያዝኩ በኢትዮጵያ ሥልጣኔን ይዤ ሸገር ገብቼ ልቀጥል በማለት ሙግት ላይ ናቸው። ብፁዕ አቡነ ሄኖክ ከመጅሊሱ ጋር የኢድ ሶላት ሰግደው ዱዓ በማድረግ ጸሎት ላይ ናቸው። አቡነ ሳዊሮስ ጭፍጨፋው የተፈጸመው በእርሳቸው ሀገረ ስብከት ቢሆንም ኬሬዳሽ…

• በቅርቡ አዲስ አበባ ይቀጥላል…