በጋምቤላ ክልል በላማዊ ሰዎች ላይ የሚደርሱ ጥቃቶች መበራከት

ከጋምቤላ ከተማ ወደ ኑዌር ዞን ይንቀሳቀስ ነበር በተባለው ተሽከርካሪ ላይ በደረሰው ጥቃት የአምስት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የአካባቢው ነዋሪዎች ለዶይቼቨለ ተናግረዋል። ጥቃቱ የደረሰው ትናንት ረቡዕ መጋቢት 18 ቀን 2016 ዓ.ም ኢታንግ ልዩ ወረዳ አካባቢ ነው። ጥቃቱን ያደረሱ ሐይሎች ግን አለመያዛቸውን ነው ያነጋገርናቸው ነዋሪዎች የገለጹት።…