አዲስ አበባ ገዳም ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በፍተሻ ታመሰ

(ኢትዮ 360 – የካቲት 2/2016) በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ ክፍለ ከተማ በተለምዶ ገዳም ሰፈር ተብሎ የሚጠራው አካባቢ በፍተሻ ሰበብ ሲታመስ ማደሩን የኢትዮ 360 ምንጮች አስታወቁ።

ፍተሻው ሲካሄድ የነበረው ደግሞ ከለሊቱ 6 ሰአት እስከ 9 ስአት እንደነበርም ተናግረዋል።

እንደሌባ በሌሊት በተካሄደው በዚህ ፍተሻ በአንድ ጠባብ ቤት ውስጥ ለፍተሻ በሚል ይገባ የነበረው የገዳይ ቡድኑ ሃይል ቁጥር ከ9 በላይ እንደነበርም አስታውቀዋል።

ደሳሳ ጎጆዎቹ እንኳን ይሄን ያህል ፈታሽ ሃይል መቻል አይደለም ለአንድም ፈታሽ ያንሳሉ ሲሉ ለሊቱን ሲሰራ ያደረውን ሽብር አንስተዋል።

ይሄ አሸባሪ ቡድን በየቤቱ እየገባ ሲበረብር ያገኘውን የኢትዮጵያ ሰንደቅ አላማ የእምዬ ሚኒሊክና የእቴጌ ጣይቱንና ከአድዋ በአል ብሎም ኢትዮጵያዊነትን ይገልጻሉ የሚባሉ አባሳትን ሁሉ መዝረፉን ይናገራሉ።

ነገር አንድ መሰመር ያለበት ነገር ይላሉ ይሄ ቡድን በየቤቱ ሲዞር ያደረው ለፍተሻ ብቻ አለመሆኑን ነው ይላሉ።

ምክንያቱ በነዛ ደሳሳ ቤቶች ውስጥ ያን ያህል ቁጥር ያለው ሃይል ሲገባ አንድም ለመዝረፍ ሁለትም ለማስፈራራትና ከዛ በላይ ግን ንጹሃንን ለመገል ነበር ይላሉ።

ምናልባትም ዛሬ ለሊት ልይ ይሄንን ግድያ ባይፈጽሙትም በቀጣይ ግን እንደሚይደርጉት የሚያሳዩ ምልክቶችን ማየታቸውን ይናገራሉ።

በየቤቱ ንብረትን ከመዝረፍና ህብረተሰቡን ከማዋከብ በዘለለ ግን ስለላ የሚመስሉና ነገ ህዝብን እንደህዝብ ለመጨረስ የተያዙ እቅዶች መኖራቸውን የሚያሳዩ ሁኔታዎችን መታዘባቸውን ሳይጠቁሙ አላለፉም።