መቐለ ዩኒቨርሲቲ ከጦርነቱ መቆም በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን አስመረቀ

[addtoany]

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ፣ የትግራይ ክልልን መነሻ አድርጎ በሰሜን ኢትዮጵያ የተካሔደው ጦርነት በሰላም ስምምነት ከቆመ በኋላ፣ የመጀመሪያ የኾነውን የተማሪዎች ምረቃ ሥነ ሥርዐት፣ ባለፈው ሳምንት ቅዳሜ አከናውኗል፡፡ 

ዩኒቨርሲቲው በዕለቱ፣ ከመጀመሪያ ዲግሪ እስከ ድኅረ ምረቃ ሦስተኛ ዲግሪ ድረስ ትምህርታቸውን በተለያዩ መስኮች የተከታተሉ፣ ከሁለት ሺሕ በላይ ተማሪዎቹን አስመርቋል፡፡ 

ከሦስት ዓመታ…