18 ቢሊዮን ብር የመሰብሰቡ ጉዞ ከሽፎ 4 አርቲስቶች ከብዙ ችግር በኋላ ሰሞኑን ወደ ሀገር ቤት ተመልሱ ።
********************************************* ቴዎድሮስ ተክለአረጋይ
👉 የቡድን መሪው እና አንድ አርቲስት እንግሊዝ ሀገር ቀርተዋል ። ( ለአጭር ቀናት ይሁን ለቋሚነት አልታወቀም )
👉 የቡድን መሪው መሳይ ሽፈራው እህት እና አንድ ሌላ ሰው በአርቲስትነት ስም ከቡድኑ ጋር ከሀገር ወጥተው እዚያው ቀርተዋል ።
👉 አርቲስቶቹ ለሁለት ወር ከአንድ ቤት ሳይወጡ በችግር ነው የቆዩት ።
👉 አርቲስቶቹ ከሁለት ወር በላይ ሲቆዩ አንድ መድረክ ብቻ ነው የሰሩት ። ሁለተኛ መድረክ ሊሰሩ ሞክረው ሳይሳካ ቀርቷል ።
👉 በእንግሊዝ ያሉ ኢትዮጵያውያን ምግብ ከየቤታቸው እያመጡላቸው ሲመገቡ ነበረ ። ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸውን አመስግነዋል ።
👉 ይህ አቶ መሳይ ሽፈራው የሚመራው ” የጥበብ ውለታ ዓለም አቀፍ ጉዞ አዘጋጅ ” ማህበር ” በአስራ አንዱም ክፍለ ከተሞች በ18 ቢሊዮን ብር ነአርቲስቶች መንደር እንገነባለን ” ብሎ ሲነሳ ለመንደሩ መስሪያ አንድ ስንዝር መሬት ሳከመንግሥት ሳይሰጠው ( ጭራሽም ሳያመለክት ) እና ምንም ገንዘብ እጁ ላይ ሳይገባ ነው ። በመጨረሻም ሁሉም ነገር እንዳልነበር ሆኗል ።
ለወደፊቱ ፦ ” የአርቲስቶች መንደር ” የሚባለው ቀልድ በአሳዛኝ መልኩ ተደምድሟል ። የ18 ቢሊየን ብሩን ቅዠት ስታራግቡላቸው የነበራችሁ ለወደፊት የተገኘውን ከመለጠፋችሁ በፊት ” እንዴት ሊሆን ይችላል ? ” ብላችሁ ሳትጠይቁ አትለጥፉ ፤ ቢከፍሉም እንኳ ።