ፓስፖርት የሚጠባበቁ አመልካቾች በሙሉ ፈጥነው ይስተናገዳሉ ሲል ተቋሙ አስታወቀ

የፓስፖርት አገልግሎት ለማግኘት ጠይቀው እየተጠባበቁ ያሉ አመልካቾችን፣ እስከ ታኅሣሥ ወር ድረስ ሙሉ በሙሉ እንደሚያስተናግድ የኢሚግሬሽን መስሪያ ቤት አስታወቀ፡፡

በኢትዮጵያ፣ የፓስፖርት አገልግሎት ማግኘት እጅግ ከባድ እንደኾነ፣ የሰነዱ ፈላጊዎች እየተናገሩ ይገኛሉ፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ፣ ባለፉት ሦስት ወራት ውስጥ ከግማሽ ሚሊዮን በላይ ፓስፖርት ታትሞ ወደ ሀገር ውስጥ እንደገባ፣ የኢሚግሬሽንና …