ርስበርስ የመዋጋት፣ የመግዳደልና የማውደም አዙሪት ይበጠስ ! = ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ

ፕሬዝዳንት ሣህለወርቅ ዘውዴ ርስበርስ የመዋጋት፣ የመግዳደልና የማውደም አዙሪት ካልተበጠሰ ዘላቂ የሰላም ግንባታ ሊሳካ እንደማይችል ተናግረዋል።

ፕሬዝዳንቷ ይህን የተናገሩት፣ የተመድ የሰላም ግንባታ ኮሚሽን ልዑካን ቡድን አባላትን በቤተ መንግሥት ትናንት ተቀብለው ባነጋገሩበት ወቅት ነው።

በውይይቱ ወቅት፣ የሠላም ግንባታ አካታችና የማኅበረሰቡን ፍላጎት ያገናዘበ ሊኾን እንደሚገባም ፕሬዝዳንቷ ጠቁመዋል።

የተመድ የሰላም ግንባታ ልዑክ አዲስ አበባ የገባው፣ በተመድና አፍሪካ ኅብረት የጋራ ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ነው።