የባሕረ ጥምቀት ይዞታዎቻችን በልማት ሰበብ እየተሸራረፉና እየተጣበቡ ነው፤ በበዓሉ ትውፊት፣ ማኅበራዊ ሚና እና በቱሪዝሙ ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ ይታሰብበት!

ከበዓል ማክበር ባለፈ የቤተ ክርስቲያን ልማትን የማይፈቅዱ የመንግሥት አካላት አሉ፤ የቤተ ክርስቲያን አመራርም፣በጥቃቅን ሥራ እየተጠመደ መብቷን ሊያስከብር አልቻለም፤ በዘላቂነት መንቀሳቀስ እንጂ ለበዓል ማጽዳት፣ ማስዋብና መጠቀም ብቻ በቂ አይደለም፤ ቤተ ክርስቲያን በቋሚ ይዞታነት ልትረከባቸው፣ልትጠብቃቸውና ልትከባከባቸው ይገባል፤ አካባቢን ያገናዘበ የማስዋብና የመጠበቅ ሥራ ለመሥራት ዝግጁነቷን ማሳየት አለባት፤ በዓሉን የሚያደምቀው የምእመኑና የወጣቱ ተነሣሽነት በይዞታ ማስከበሩም ይጠናከር፤ *** ጃንሜዳ፣ በየአቅጣጫው …