” … መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉት 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ናቸው ” – ቃሊቲ ማረሚያ ቤት

” … መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉት 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ናቸው ” – ቃሊቲ ማረሚያ ቤት

ከቃሊቲ ማረሚያ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ነበሩ የተባሉ ታራሚዎች በቁጥጥር ሥር መዋላቸው ተሰምቷል።

ከቃሊቲ ማረሚያ ቤት  መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉር የከባድ ውንብድና ወንጀል ፍርደኛ ታራሚዎች መሆናቸው ተነግሯል።

ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ጥበቃና የደኅንነት አስተባባሪ ኢንስፔክተር ድሪባ ሰንበታ ለኤፍ ቢ ሲ የሰጡት ቃል ፦

” ትናንት ሌሊት 10 ሰዓት ከ30 ላይ መሬት ቆፍረው ሊያመልጡ ሙከራ ያደረጉ 10 የከባድ ውንብድና ፍርደኛ ታራሚዎች ላይ ማረሚያ ቤቱ ባደረገው ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል።

ለማምለጥ ሙከራ ካደረጉ ፍርደኞች መካከል ከዚህ በፊት #አምልጦ ከጣልያን ሀገር በኢንተርፖል ተይዞ የመጣ ታራሚ ይገኝበታል።

ሌሎችም በተደጋጋሚ ከጤና ጣቢያ ፣ከመኪና ላይ ጭምር ለማምለጥ ሞክረው የተያዙ ፍርደኞች አሉ።

ማረሚያ ቤቱ  ዛሬ በተለያዩ ፍርድ ቤቶች ቀጠሮ የነበራቸው ታራሚዎችን አጅቦ በማቅረብ መደበኛ ስራውን ሲሰራ ውሏል።

ታራሚዎቹ  ከመሰል ድርጊት እንዲቆጠቡ ተገቢ የሆነ  የክትትልና የቁጥጥር ስራው ይቀጥላል። “