በቀዶ ሕክምና ለማዋለድ የሞባይል መብራትን የሚጠቀሙት የሱዳን ሐኪሞች

ከአንድ ወር በላይ ያስቆጠረው የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በዋና ከተማዋ ካርቱም ሳይቀር ለወላድ እናቶች በእጁጉ አስከፊ ሆኗል። በርካታ የጤና ባለሙያዎች አገሪቱን ለቀው ተሰደዋል፤ በአሁኑ ወቅት በሱዳን ውስጥ የቀሩት ስፔሳሊስት ሐኪሞች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። በዚያ ላይ ውሃ እና መብራትን የመሳሰሉ መሠረታዊ አቅርቦቶች በአብዛኛው ጊዜ ተቋርጠው ነው የሚገኙት። ይህ ችግር ደግሞ በሕክማና ተቋማት ው…