አፈናው ቀጥሏል ፡ የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ ታሰሩ

May be an image of 1 personመጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ በጸጥታ አካላት ተይዘው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ውስጥ ይገኛሉ !
የማኅበረ ቅዱሳን የሕዝብ ግንኙነት እና ትብብር አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት መጋቤ ብርሃናት ቀሲስ ሙሉቀን ብርሃኑ ዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2015 ዓ.ም ከቤታቸው ወደ ሥራ ብለው ከወጡ በኋላ ስልካቸው የተዘጋ እና መገኘት ያልቻሉ ሲሆን ከምሽቱ 12:00 ሰዓት በኋላ ግን በጸጥታ አካላት ተይዘው ወደ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን መወሰዳቸውን ማኅበረ ቅዱሳን ከቤተሰቦቻቸው ማረጋገጥ ችሏል።
በተመሳሳይ መ/ር ተሾመ በየነ ገላን አካባቢ በሚገኝ ፖሊስ ጣቢያ ውስጥ እንደሚገኙ ታውቋል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል